Logo
FastMereja
ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም የወጣ አልበም ሶሻል ሚዲያውን ተቆጣጥሮታል፣ ሮቤል ሚደቅሳ የተሰኘው ድምጻዊ "ከበር አፍ" የተሰኘ የሙዚቃ አልበሙ በርካታ ሰዎች የአድናቆት ብዕራቸውን እንዲያነሳ አድርጓቸዋል።

ስለ አልበሙ ምን አሉ?

📌 "ይህን አልበም እስካሁን ካልሰማችሁ ቀረባችሁ" የስነ ልቦና ባለሙያ ቃልኪዳን ሻረው

📍"ሮቤብ ሚደቅሳ ከዘፈንህ ጋርማ ሙጣንጢም አስደርገህበታል እንጂ እንዴት 24/7 ቁጭ ብዬ ያንተን ዘፈን እስማለሁ" ሜላት ንጉሴ

📌 "በጣም ሰማሁ ሰማሁ ሰማሁ ከወጣ እለት ጀምሮ አልበሙን የሰማሁት እስካሁን ለመፍረድ ተቸግሬ ነበር አሁን ወሰንኩ። እንኳን ደስ ያላቹህ" እስማኤል ሃሺም

📍"የሮቤል ሚደቅሳ አልበም ሙዚቃ/ ኪነጥበብን በቅጡ ማጣጣም ለሚችሉ ጥሩ ጆሮ ላላቸው የተሰራ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ።" ጋዜጠኛ ኤርሚያስ በጋሻው

📌 "ጆሮን አልፎ በልብ የሚደመጥ የጥበብ ስንቅ" ኢፎይ አዲስ

📍"ረግተህ ስላረጋኸን ያለ ድምድምታ ያለ ኳኳታ ሙዚቃን እንድናጣጥማት ስላደረከን እናመሠግናለን" ሀሌታ

📌 "በዚህ ዘመን ሁሉም ትራክ በፍቅር የሚደመጥለት አልበም ብዙ የለም። Robel Mideksa ግን ታሪክ ሰርቷል።" ሱአድ አህመድ

📍"ስክን ያል፣ የሚያረጋጋ፣ ከጆሮ አልፎ በልብ የሚሰማ፣ ሁሉም ነገሩ አዲስ የሆነ፣ ከግርግር የሚያስወጣ፣ ክሰትት የሆነ አልበም ነው" ፂዮን ታምራት

📌 "እንደህጻን ገላ የሚለሰልስና የሚጣፍጥ አልበም! ለካ ጩኸት ሳይበዛም እንዲህ ልስልስ ያለ ሙዚቃ መስራት ይቻላል!" ያደል ትዕዛዙ

📍"በእኔ ጆሮ ስገመግመው የራሱን ስፍራ አጥሮ፣ በራሱ መቆም የሚችል ኩልል፣ እርግት፣ ፍስስ ያለ ደም ግባት ያለው አልበም ይዞ መጥቶልናል፡፡" አወቀ አበበ

📌 "Robel Mideksa የሚባል ሰውዬ ምን አደረገኝ?
የማላውቀውን ብዙ ነገር አስናፈቀኝ፤ አልቅሽ አልቅሽ አለኝ፤ ማማር ባር ባር ይላል እንዴ? ውበት ልብ ይበላል እንዲህ? በእግዚአብሔር እቀፉኝ ሮቤል ግን ትችላለህ ገብርኤልን" ኤልሳ ሙሉጌታ

📍"ድምፃዊ ሮቤል ሚደቅሳን አዲስ የሙዚቃ አልበም ሰምቶ ከ85% በላይ የሆነው የሙዚቃ አድማጭ በአንድ ድምፅ በተመሳሳይ አቋም አድናቆትን መቸሩ የሚያጠራጥር አይመስለኝም ደግሞም መደነቁ አይገርምም ::" ሴም አማኑኤል

📌 "የሚዲያ ጋጋታ ሳይኖር ፡ ሙዚቃዬን ስሙልኝ ብሎ ሳይቀሰቅስ ፡ ይሄን ያህል ሚሊዮን ብር አውጥቻለሁ ብሎ ሳይሰክስ ፡ ግብዝ ሳይሆን ፡ ለጆሮ ፈውስ የሆነ ፡ በዝምታ ፅድት ያለ አልበም ጀባ ነው ያለን🤞
ፋርማሲ ላይ ጠዋት አንድ ፤ ምሳ ሰዓት አንድ ፤ ራት ላይ አንድ እየተባለ መታዘዝ ያለበት ሙዚቃ 🎶" ኤሊያስ አዛናው

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.