በጋምቤላ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተነገረ
#ethiopia | በጋምቤላ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ቀደም ካሉት ጊዜያት አንፃር አሁን ላይ መቀነሱን የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት አስታውቋል።በጽህፈት ቤቱ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡላ ድንጉር ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በክልሉ የነበረው የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኝ ነበር።
ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭትን በማስመዝገብ ክልሉ ቀዳሚ እንደነበር ገልፀው ከሁለት አመታት ወዲህ ግን ከአዲስ አበባ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ እንደቻለ አስረድተዋል።
ስርጭቱ እ.አ.አ በ2023 ላይ ከነበረበት 3 ነጥብ 14 በመቶ ባለፈዉ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት መሰረት ወደ 3ነጥብ 09 በመቶ መቀነሱ ተረጋግጧል።
የክልሉ መንግስት ለጉዳዩ ልዮ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ፣ የቫይረሱን ስርጭት በመግታት በኩል የአጋር አካላት ድጋፍ መኖር እንዲሁም ለማህበረሰቡ የግንዛቤ መፍጠር ስራዎች መሰራታቸው ለዚህ ውጤት አስተዋፅኦ አበርክቷል።
አሁን ላይ በክልሉ ያለው የበሽታው ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም በሚፈለገው ልክ መሻሻሎች አላሳየም። በክልሉ የኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት አምራች ኃይል በሆኑት ወጣቶች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት አሁንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል።
#dagu

6 months ago