Logo
SeledaPost
“የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደ ፀጉር ቅማል አንድ በአንድ እናራግፋለን” - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

“የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደ ፀጉር ቅማል አንድ በአንድ እናራግፋለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ክብረ በዓል በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሲከበር ባደረጉት ንግግር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ወቅት “የሀገርን መሻት እና የባዳን ክፋት መለየት ይጠበቅብናል” ያሉ ሲሆን “ባዳ በክፋት የእኛን መሻት ለማጨለም ሲነሳ፤ ኢትዮጵያውያን ለባዳ ፍላጎት መሳሪያ እንዳንሆን” ሲሉ አሳስበዋል።

“እርስ በርስ መተሳሰር ሲገባን፣ ክፉ እሳቤ ያለውን የባዳን መሻት በውስጣችን እንዳናስገባ እና በታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን፤ ኢትዮጵያውያን ልብ ገዝተን ሰላማችንን እናጽና” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም “በንግግር እንመን። በተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት እንስራ፣ ሌብነትን እንጠየፍ። የሀገር ጥቅም እና የህዝቦቻችን ክብር እናስቀድም። ለዘመናዊነት፣ ለለውጥ ክፍት እንሁን። ሉዓላዊነታችንም በሁሉም መስክ እናሳካ” ብለዋል።

“ኢትዮጵያ በብዙ ተስፋ የተሞላች ሀገር መሆኗን” ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም “ብዙ አስደናቂ ጅምሮች እና ውጤት እያሳየች፣ እየተመነደገች፣ እያንሰራራች ያለች ሀገር ናት” ሲሉ ገልፀዋል።

“ይህ መልካም ጅምሮ በፈጣሪያችን የሚደገፍ ቢሆንም፣ በሰይጣን ትጋት ቀን ከሌት ለማደናቀፍ ሙከራዎች ይደረጋሉ” ሲሉ ገልፀው ሆኖም “ማንኛውም ፈተና፣ ማንኛውም ትንኮሳ፣ ማንኛውም የክፉ ሀሳብ ኢትዮጵያን ከብልጽግና ማቆም አይችልም” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

Via As

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.