“ማንኛውም ትንኮሳና ፈተና ኢትዮጵያን ከብልጽግና ጉዞ ማስቆም አይችልም”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ማንኛውም ትንኮሳና ፈተና ኢትዮጵያን ከብልጽግና ጉዞ ማቆም አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማንኛውም ፈተና፣ ትንኮሳና ክፉ ሃሳብ ኢትዮጵያን ከብልጽግና ማቆም አይችልም።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ጠላቶች አንድ በአንድ እናራግፋለን ብለዋል።
ከአባቶቻችን በደም የወረስነውን ነጻነት በብልጽግና ማጽናት ከዚህ ትውልድ እንደሚጠበቅ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛ ከጨለማ ወደ ንጋት እየተሸጋገረች መሆኑን ገልጸዋል።
ብልጽግናን ማሳካት ፈታኝ መሆኑን በመግለጽ፤ የወረስነውን ነጻነት ብቻ ሳይሆን የተሸከምነውን የትውልድ አደራ ማሰብ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ችግሯን ብቻ ሳይሆን አቅሟን ማየት አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ትውልድ ችግሯን ብቻ ሳይሆን አቅሟን ፍልፍሎ የማየትና የማውጣት ብቃት አለው ብለዋል።
ከኢትዮጵያ መቀበል ብቻ ሳይሆን መስጠትም እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ የጸናች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የአገርን መሻትና የባዳን ክፋት መለየት እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፤ ኢትዮጵያዊያን ለባዳ ፍላጎት መሳሪያ መሆን እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊያን ቀልብ ገዝተን ሰላማችንን እናጽና ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የአገርን ክብርና የዜጎችን ጥቅም እናስከብር ብለዋል።
ኢትዮጵያ በብዙ ተስፋ የተመላች አገር መሆኑኗን ጠቅሰው፤ አስደናቂ ጅማሮና ውጤት እያሳየች መሆኑንም ገልጸዋል።
#ጋዜጣ_ፕላስ

6 months ago