የኢትዮጵያ ወር በኩሪፍቱ ተከበረ
(በጌጡ ተመስገን እና ዕዝራ እጅጉ)
#ethiopia | የኢትዮጵያ ወር ፣ የተባበሩት መንግሥታት እና ኢትዮጵያ ግንኙነት የመሠረቱበት 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል በኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ትናንት ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተከብሯል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ኩሪፍቱ ሪዞርት ትብብር በተዘጋጀው በዚህ መርሀ- ግብር አዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ አገራት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የዓለምአቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አሰምተዋል።
በንግግራቸውም፣ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካ አገራት ባህልና እሴት በማስተዋወቅ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል። አያይዘውም፣ በኢትዮጵያና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል የነበረውን ያለፉትን 80 ዓመታት ዘክረዋል።
የኢትዮጵያ ወር ተብሎ የተከበረውና ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው የመዝጊያ መርሐ -ግብር የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት የማስተዋወቅ ግብ የሰነቀ ሲሆን ኢትዮጵያ እንደ አገር ያላትን የቱሪስት መዳረሻዎች በማስተዋወቅም በዘርፉ ያለውን የኢኮኖሚና የህዝብ ለህዝብ ትብብርና ግንኙነት ያጠናክረዋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ቪሌጅ የኩሪፍቱ ሪዞርት መሥራች እና ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው ኢትዮጵያ መልክአ ምድሯ የሚመች የአየር ንብረቷም ተስማሚ መሆኑን ገልፀው እንኳን ለኢትዮጵያ ወር አደረሳችሁ፣ ወደ ኩሪፍቱም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ኢትዮጵያ መጎብኘት ያለባት የቱሪዝም መስህብ መሆኗንም ተናግረዋል።
የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡም ከመንግስታዊና የግል ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪው አብሮ ለመሥራት ጥሪ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ሲመሠረት ከመሥራች አገሮች አንዷ ነበረች። ዘንድሮ 80 ዓመት የሞላው የመንግሥታቱ ድርጅት በብዙ ውጣውረድ አልፎ እዚህ የደረሰ ሲሆን ኢትዮጵያም ከድርጅቱ ጋር ያላትን ሁለገብ ግንኙነት በማጠናከርና አፍሪካዊ አጀንዳዎችን በማጉላት ድርሻዋን እንደምትወጣ በመድረኩ ተገልጿል።
በዝግጅቱ የአገር ፍቅር ትያትር የባህል ቡድን በመገኘት ለምሽቱ ድምቀት ሰጥቶታል። መሰል የባህል ምሽቶች ቢደረጉ የአዲስ አበባን ገጽታ በመገንባት ረገድ የራሳቸው አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ይታመናል።

8 months ago