ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞች፣ ከዛሬ ኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው እንደሚሰማሩ ተገለጸ
#ethiopia | የገቢዎች ቢሮ ፤ የተመደበለትን ከ1ዐዐ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመጠቀም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመቀናጀት የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክትን (Body Worn Camera Project) አልምቶ በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መሸጋገሩን አሳውቋል።
በዚህም መሠረት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከዛሬ ረቡዕ ኅዳር 24 ጀምሮ ግብር ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ የሕግ ማስከበርና የቁጥጥር ሥራዎችን የሚያከናውኑ ሠራተኞቹ፣ ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመለት ዩኒፎርም በመልበስ እንደሚሰማሩ አስታውቋል።
ይህ የካሜራ ቴክኖሎጂ የቁጥጥር ባለሙያዎች ቁጥጥራቸውን በድምፅና በምሥል በመቅረፅ በቀጥታ ለዋና መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች እንደሚልኩ ቢሮው ገልጿል።
በመሆኑም በዋና መሥሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚገኙ ባለሙያዎች፣ በቡድን የሚንቀሳቀሱ የቁጥጥር ባለሙያዎች እያንዳንዳቸው፦
- በየትኛው አካባቢ ቁጥጥር እያካሄዱ መሆናቸው (Location Tracking)
- ከግብር ከፋዮች ጋር የሚያደርጓቸውን ንግግሮች በድምጽ እና በምስል የሚከታተሉ መሆናቸውን አሳውቋል።
ይህም በግብር ከፋዮች ዘንድ በተዳጋጋሚ የሚነሱ ብልሹ አሠራሮችን ለመቅረፍ እንደሚያስችል የጠቆመው ቢሮው፣ ከመርካቶ ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ የገበያ ቦታዎች የሚነሱ ለዓመታት የዘለቁ ቅሬታዎቻቸውን ለመቅረፍ እንደሚያስችል ገልጿል።
የሌብነትና ብልሹ አሠራሮችን ከመከላከል ባሻገር፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ቅልጥፍና በማጎልበት ዘንድሮ በከተማ አስተዳደሩ ለመሰብሰብ የታቀደውን 350 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት እንደሚያስችልም ጠቁሟል።#ሪፖርተር

7 months ago