Logo
SeledaPost
የገቢዎች ሠራተኞች ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ሊለብሱ ነው‼️

ግብር ከፋዮችን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞች፣ ከኅዳር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ካሜራ የተገጠመበት ዩኒፎርም ለብሰው እንደሚሰማሩ ተነግሯል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ የተመደበለትን ከ1ዐዐ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመጠቀም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት (ኢንሳ) ጋር በመቀናጀት የቦዲ ዎርን ካሜራ ፕሮጀክትን (Body Worn Camera Project) አልምቶ በማጠናቀቅ ወደ ተግባር ተሸጋግሯል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከዛሬ ረቡዕ ኅዳር24 ጀምሮ ግብር ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ የሕግ ማስከበርና የቁጥጥር ሥራዎችን የሚያከናውኑ ሠራተኞቹ፣ ቪዲዮ ካሜራ የተገጠመለት ዩኒፎርም በመልበስ እንደሚሰማሩ አስታውቋል።

ይህ የካሜራ ቴክኖሎጂ የቁጥጥር ባለሙያዎች ቁጥጥራቸውን በድምፅና በምሥል በመቅረፅ በቀጥታ ለዋና መሥሪያ ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች እንደሚልኩ ቢሮው ገልጿል።

በመሆኑም በዋና መሥሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚገኙ ባለሙያዎች፣ በቡድን የሚንቀሳቀሱ የቁጥጥር ባለሙያዎች እያንዳንዳቸው በየትኛው አካባቢ ቁጥጥር እያካሄዱ መሆናቸውን (Location Tracking)፣ እንዲሁም ከግብር ከፋዮች ጋር የሚያደርጓቸውን ንግግሮች በድምፅና በምሥል የሚከታተሉ መሆናቸውን ታውቋል።

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.