12ኛው ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ተካሄደ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ያዘጋጀው 12ኛው ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነሥርዓት በታላቁ ቤተመንግሥት በትናንትናው እለት ተከናውኗል::
በሥነሥርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት እና የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚ/ር አቶ መላኩ አለበል፣ የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ሚ/ር ድኤታ አቶ እንዳለው መኮንን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንዲሁም የኩባንያ ባለቤቶች፣ ሥራ አስፈጻሚዎችና ልዩልዩ እንግዶች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን በጥራት ሽልማት ውድድሩ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ፋብሪካ ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሃይንከን ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ አሸናፊዎች ሆነዋል::
በተጨማሪም ለሦስት ተከታታይ ጊዜያት አንደኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫን በማሸነፉ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ፋብሪካ ልዩ የልህቀት ዋንጫ አሸናፊ በመሆን ከክቡር ፕሬዚዳንት እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል::
#ኹነት

7 months ago