''የምንሠጠው ስለተረፈን አይደለም'' ዶ/ር ፍቅረማሪያም ጉደታ
📌ያለጊዜያቸው የተወለዱ (Preterm Birth) ጨቅላ ህፃናትን ቀን በማስመልከት ግንዛቤ ማስጨበጫ ተደረገ
#ethiopia | ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ለ25ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉ ምክንያት በማድረግ ከሚያከናውናቸው 25 የበጎ አድራጎት ሥራዎች መካከል አንዱን ትልቅ መርሐ ግብር ዛሬ አከናውኗል።
የመርሐ ግብሩ ዋና ትኩረት ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ህፃናትን በተመለከተ ግንዛቤን ማስጨበጥ እና ድጋፍ ማድረግ ነው ተብሏል።
የሆስፒታሉ መሥራች የሆኑት ዶክተር ፍቅረማሪያም ጉደታ እንደገለጹት፣ ''የምንሠጠው ስለተረፈን አይደለም ፤ሳይኖረንም እንሰጣለን ፤ መቆረስ የኛ መርህ ነው'' ብለዋል።
ይህንኑ ቁርጠኝነት ለማሳየት ሆስፒታሉ ባለፈው ሐሙስ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ያካሄደ ሲሆን፣ 20 የሆስፒታሉ ባልደረቦች ደም መለገሳቸውን ሲስተር ቅድስት ሀብተማሪያም ተናግረዋል።
ዛሬ በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የጨቅላ ሕፃናት ሠብ ስፔሻሊስት ዶክተር ሙሉዓለም ገሠሠ ያለጊዜ መወለድ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሊያጋጥም እንደሚችል ገልጸዋል።ዶ/ር ሙሉዓለም አክለውም በጉዳዩ ላይ ለወላጆች እና ለኅብረተሰቡ የባለሙያ ምክርና ግንዛቤ ማስያዝ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ የደም ልገሳ በጎ አድራጎት መደረጉም “አደራችንን ለመወጣት” ነው ሲሉ አስረድተዋል።
በዛሬው መርሐ ግብር የሆስፒታሉ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ የተገኝች ሲሆን ''ከሆስፒታሉ ጋር ያስተዋወቀን አጋጣሚ አብሬያቸው እንድሰራ አስችሎኛል'' ብላለች።
በዝግጅቱ ላይ አርቲስት ሄኖክን ጨምሮ የሕክምና ባለሙያዎች እና ወላጆች መሳተፍቸው በስፍራው ተገኝተን አይተናል።
"ወርቃማ ልቦች ፣ አገልጋይ እጆች!" የሚል መርህ ያነገበው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የሕክምና አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶችን መስጠቱን እንደሚገፋበት አሳውቋል።

7 months ago