የአለምአቀፍ የሴቶች መብት ስምምነት በሀገራችን የህግ ማእቀፍ እይታና አፈጻጸም አንጻር ያለው ክፍተት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ ወ/ሮ ቃልኪዳን አወቀ በማናቸውም ፌደራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ 0910683246
መግቢያ #ethiopia | ኢትዮጵያ የሴቶችን መብት ከማስከበር አንጻር የአለምአቀፍ ስምምነቶችን በማድረግ ቀዳሚ ተግባራት ፈጽማለች። በኢ.ፊ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 13/2/ መሠረት የህጋችን አካል በማድረግ የራሷንም ህግ በማውጣት የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገች ነው። ይሁን እንጂ ህጉን በማስፈጸምም ሆነ መብቶቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ከማስጠበቅ አንጻር ክፍተቶች የሚታዩ ሲሆን ይህን በዚህ አጭር ጽሁፍ የሚታይ ግንዛቤም ለማህበረሰቡ ለማሳደግ ቀርቧል።
. ፆታዊ ጥቃት ምንድን ነው?
ፆታዊ ጥቃት በሰዎች ላይ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ተብለው ሊከፈሉ ይችላሉ።
1.1 የሥነ-ልቦናዊ ጥቃት፡-
በቃላት ወይም ሞራል በሚነኩ አባባሎች ማሸማቀቅ እና ማስፈራት፣ በአካላዊ ጥቃት ወቅት በሚደርስባቸው የአካል ጉዳት ወይም ያልተፈለገ እርግዝና እና የጤና ጉድለት ምክንያት የሚከሰት የሥነ ልቦና አለመረጋጋት፣
1.2 ባህላዊ ጥቃት፡-
በባህል የሚፈፀም የውርስ ጋብቻ፣ ያለመውለድ ችግር ሴትን ብቻ ተጠያቂ አድርጎ በመውሰድ ከትዳር መፈናቀል፣ ልጆችን በማሳደግ ረገድ ሴቶች ከፍተኛውን ድርሻ መሸከም፣ በልጅነት ተገዶ መዳር፣
1.3ኢኮኖሚያዊ ጥቃት፡-
ሴቶችን በኢኮኖሚ ለመቆጣጠር የፋይናንስና የሃብት አማራጮችን መገደብ፣
1.4 ወሲባዊ ጥቃት፡-
ሃይልን በመጠቀም ያለፍላጓቷ የሚፈፀም ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊትና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊትን የመሰሉ ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችና ትንኮሳዎችን ፣ አስነዋሪ ለሆኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ድርጊቶች ማስገደድ
2. የፆታዊ ጥቃት የሚያስከትላቸው ችግሮች
2.1 የጤና የአካል ጉዳት፣ ሞት፣ ፌስቱላ፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች መያዝ፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም እና በወሊድ ወቅት ለአደጋ መጋለጥ፡፡
2.1 የሥነ-ልቦናዊ ሀፍረት፣ ፀፀት፣ ድብርት፣ ፍርሃት፣ ራስን መጥላት፣ በራስ ያለመተማመን፣ አለመረጋጋት፣ ብቸኝነት፣ መገለልና መድሎ፣ የአእምሮ ህመም፣ ተስፋ መቁረጥና ሱሰኛነት፡፡
2.3 ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ከትምህርት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነት ራሳቸውን ማገለል፣ በኢኮኖሚ አምራችነት መቀነስና ኑሮቸውን በኢኮኖሚ ጥገኝነት መቀጠል፣ የቤተሰብ መበተንና መቃወስ፣ ለስደት፣ ለሌሎች በርካታ ሴቶችና ህፃናት ስጋት፣ አለመረጋጋት የበዛበት ማህበረሰብ እንዲፈጠር፡፡
2.4 በፍትህ ስርዓቱ ላይ ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ተገቢውን የሕግ ምላሽ እና ከለላ በማያገኙበት ጊዜ በሀገሪቱ ሕግና ሥርዓት ላይ ህብረተሰብ መፈጠር እና ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች ለህግ አካላት ሪፖርት ከማድረግ መቆጠብ፡፡
2.5 የፆታዊ ጥቃት መንሰኤዎች ማህበረሰቡ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት መቀበሉ፣ ኃላ ቀር የሆነ አስተሳሰቦች፣ ጎጂ ልማዳዊ ልምዶች፣ ማህበረሰቡ ስለ ሥርዓተ-ፆታ ያለው ግንዛቤ አነሳ መሆን፣ የሴቶችን መብቶች የሚያስከበሩ ህጎች አፈፃፀም አናሳ መሆን፣ የመጠጥ፣ የእጽና የተለያዩ ሱሶች ተጠቃሚነት፣ ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞች መስፋፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
2.6 ፆታዊ ጥቃት በማንና የት ይፈፀማል?
በቤተሰብ አባል፣ በጎረቤት፣ ጓደኛ፣ በትዳር አጋር፣ በሀይማኖት አባቶች፣ በመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች በቅርብ በሚታወቁና በማይታወቁ ሰዎች፣
ጥቃቱ በማንኛዉም ቦታ የሚፈጸም ነዉ፡፡ በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት፣ በመንገድ፣ በሥራ ቦታ፣ ገበያ እና በሌሎች፡፡
2.7 ፆታዊ ጥቃትን ለማስቆም የተወሰዱ እርምጃዎች
አለም አቀፋዊ እርምጃዎች፡-
3. የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን 3. ለመከላከልና ለሴቶችና ህፃናት በቂ ጥበቃ ለመስጠት ሰነዶችን፣ መግለጫዎችን እና ስምምነቶችን አፅድቋል፡፡
3.1 ሁሉ ዓቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ/ Universal declaration on human right, 1948/
ይህ ሰነድ የሰዎች እኩል የሆነ ሰብዓዊ ክብርና መብትን እና ሁሉም ሰው ከአካላዊ ስቃይ ኢሰብአዊና ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ የመጠበቅ መብት እንዳለው አካቶ የያዘ አለምአቀፍ ስምምነት ነው፡፡
3.2 አለምአቀፍ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ስምምነት / International covenant on civil and political rights, 1966/
በዚህ ስምምነት ላይ በህይወት የመኖር መብትን፣ ከምንም አይነት አድልዎ የመጠበቅ መብትን፣ የአካል ደህንነትንና ነጻነት መብትን እውቅና የሰጠ ሰነድ ነው፡፡
3.4 አለምአቀፍ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶች ስምምነት/ International covenant on economic, social and cultural rights, 1966/
ይህ ስምምነት ከምንም አይነት አድልዎ የመጠበቅ መብትንና ሚዛናዊና አመቺ የስራ ቦታ የማግኘት መብትን ያካተተ ነው፡፡ ይህ በተዘዋዋሪ ሴቶች በስራ ቦታ ሊፈጸምባቸው ከሚችለው ወሲባዊ ትንኮሳ ጥበቃ ያደርጋል፡፡
3.5 በሴቶች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት ልዩነት ወይም አድሎ ለማስወገድ የወጣ ስምምነት (CEDAW, 1979)
ይህም ስምምነት በፆታ ላይ የተመሰረተን አድሎኣዊ ልዩነት፣ ገደብ ወይም ማግለልን በመከልከል አባል መንግስታት በማናቸውም መልኩ የሚፈፀም ልዩነት ለማስወገድ የሚያስችል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስገድዳል፡፡
3.6 የአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነድ አንቀፅ 4/1 ላይ ማንኛውም የህብረቱ አባል ሀገራት
የሴቶችን እኩልነት የማህበር ግዴታ እንዳለባቸው በመርህ ደረጃ ያስቀምጣል፡፡
3.7 አፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች መብቶች ቻርተርና የአፍሪካ ሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል/ Protocol to the African charter on human and people’s rights on the right of women, 2003/
ይህ ፕሮቶኮል በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሏዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ የወጣው አለም አቀፍ ስምምነት ከያዛቸው ድንጋጌዎች ጋር ተመሳሳይ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን የአፍሪካን ሴቶች ነባራዊ ሁኔታ ማለትም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚደርስባቸውን በደልና የስርዓተ-ጾታ ችግሮች ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
3.8 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት
በአንቀጽ 35/4 በሴቶች ላይ አካላዊ አእምሮዊ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶች፣ ህጎችና ልምዶች አንዲወገዱ መንግስት ኃላፊነት እንዳለበት ይገልፃል፡፡
3.9 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ህግ
የወንጀል ህጉ ፆታዊ ጥቃት የወንጀል ድርጊቶች መሆናቸውን በመደንገግ ሊያስቀጡ የሚችሉትን ቅጣት በማካተት ደንግጓል፡፡ ለመጥቀስ ያህል በግብረ-ሥጋ ነፃነትና ንፅህና ላይ የሚፈጸሙ ወጀሎችን (አንቀጽ 620-628)፣ ለተፈጥሮ በተቃራኒ ባህሪይ የሆኑ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ድረጊቶችን በተመለከተ (አንቀጽ 629-632)፣ የተለያዩ ጎጂ ልማዳዊ ድረጊቶችን (አንቀጽ 561-562) ፣ ጠለፋ (አንቀጽ 587-590)፣ ያለእድሜ ጋብቻ አንቀጽ (647-648)፣ አካል ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀጽ 555-560)፣ ግንኙነት ባላቸዉ ሰዎች መካከል የሚፈጸም ጥቃት (አንቀጽ 564)፣ በሴቶችና ህጻናት መነገድ (አንቀጽ 597-599፣ የዝሙት ተግባር (አንቀጽ 635-638) በህጉ ለሴቶች መብትና ደህንነት ጥበቃ የሰጡ
ድነጋጌዎችን ናቸው፡፡
3.10 የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992
በጋብቻ፣ በልጅ አስተዳደግ፣ በሃብትና ንብረት አስተዳደር፣ በፍቺ ጉዳዩች ላይ ለሴቶች እኩልነት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡
4. ከፍትህ ሚኒስትር እና ከፖሊስ ኮሚሽን ምን ይጠበቃል?
4.1 ወንጀልን መከላከል
ህብረተሰቡ “ፆታዊ ጥቃት መከላከል የእኔ ጉዳይ ነው፤ ይመለከታኛል” ይል ዘንድ በህዝብ አደረጃጀቶችን በመጠቀም እና በተለያዩ የመገናኛ ዜዴዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ በመቀየር ፆታዊ ጥቃት እንዳይፈፀም የመከላከል ስራ መስራት፡፡
እንዲሁም ወንጀልን ለመከላከል ከሚረዱ ዘዴዎች መካከል ወንጀል ፈፅመዉ ሲገኙ ቅጣት ከሚተላለፍባቸዉ ሰዎች ህብረተሰቡ ትምህርት በመዉሰድ ከወንጀሉ እንዲቆጠቡ በማድረግ ነዉ፡፡
የወንጀል ህግ ግቡም ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተዉ ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማርያ እንዲሆን ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ እርምጃዎች እንዲወሰዱባቸዉ ለማድረግ ነዉ፡፡
ከዚህ አንፃር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተቋም በአዋጅ የተሰጠዉን ስልጣን በመጠቀም በሴቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ከፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ በማድረግ ክስ በመመመስረት እና የድርጊቱን ፈፃሚዎች ለፍርድ ቤት በማቅረብ ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት እንዲወሰን በማድረግ ህብረተሰቡ የፍርድ ቤቱን ቅጣት ውሳኔ እንዲያውቅ እና ራሱን ከድርጊቱ እንዲቆጥብ ማድረግ፡፡
4.2 ምላሽ ከመስጠት አንፃር
በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ምድብ ጽ/ቤቶች እና በድሬደዋ ምድብ ጽ/ቤት የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት ወንጀሎችን ተገቢውን ምርመራን ከፖሊስ ጋር በመሆን ያካሄዳል ምርመራዉንም ከተጠናቀቀ በኃላ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ በማቅረብ እና ክርክር በማድረግ ወንጀል ፈፃሚው እንዲቀጣ የማድረግ ስራን ይሰራል፡፡
4.3 ከፍርድ ቤቶች ምን ይጠበቃል?
ፍርድ ቤቶች በእርግጥ ኃላፊነታቸው በህግ በፍሬ ነገርና በማስረጃ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም ይህን ከማድረግ አንጻር አስፈላጊና ተገቢነት ያላቸውን የህገመንግስት፣ ስለሴቶች የተደረጉ አለምአቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም የወንጀል ህጉንና አግባብነት ያለቸውን ህጎች መመሪያዎች መሠረት ባደረገ መልኩ ለሴቶች የተሰጠውን መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር አስፈላጊውን ማጣራት በማድርግ አስተማሪና ለሌላውም አስተማሪ የሆነ የቅጣት ውሳኔ ሊተላለፍ ያስፈልጋል።
5. የሴቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ለመከላከል የእኩልነት መብት ከማረጋገጥ አንጻር የአፈጻጸም ችግሮች
ሴቶች በህግ የተሰጣቸውን መብት ከማስጠበቅ አንጻር በተለይም በክልል በገጠር ውስጥ ከሚደርሱ ጥቃቶች አንጻር ህጎችን ተግባራዊ ለማድረግ ገና ሰፊ ስራዎች የሚጠበቅ ሲሆን ህጻናት ሴቶች እንኳን ከሚደርስባቸው ጥቃት ህይወታቸውን ቢያጡም እንኳን ይህን አድራጊው አካል ላይ በወንጀል የተቀመጠው ቅጣት የእድሜ ልክ ወይም እስከ 25 አመት ጽኑ እስራት ብቻ መሆኑ በሀገራችን ያሉ ህጎች ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን የሴቶችን መብቶቾ በህጎቿ አቅፋ የመተግበር ላይ ልልነት የሚታይ መሆኑን ማስተዋል የሚቻል ሲሆን ከዚህ ረገድ ህግ አውጪዎች ሊያስቡበት የሚገባ ነው።
6. ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን የአለምአቀፍ የሴቶች መብት ስምምነትን በተመለከተ በህጎቿ አንድ አካል አድርጋ ከመተግባር አንጻር የህጉ ልልነት እንዲሁም በህጉ የወጣውን የሴቶች መብትን ለሴቶች በመቶርገም እውን ከማድረግ አንጻር ሰፊ ስራ የሚጠበቅ በመሆኑ ህግ አውጪው፣ህግ አስፈጻሚው እንዲሁም ተርጓሚው ትኩረት ሰጥት ሊሰራ የሚያስፈልገው ነው።

10 months ago