Logo
Getu Temesgen
የአዊ ብሄ/አስ - አባይ ባንክ የሁለትዮሽ ስምምነት
#ethiopia | የአዊ ብሄ/አስ የመንግሥት ሠራተኞችን የረጅም ጊዜ የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የውል ስምምነት ከአባይ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

የአባይ ባንክ -የአዊ ብሄ/አስ የመንግስት ሰራተኞች ሁለትዮሽ ስምምነቱ የቤት መግዣ፣የመኪና መግዣ እና ለቤት ቁሳቁስ መግዣ የረጅም ጊዜ የብድር አቅርቦት መሆኑ ተነግሯል።

የአዊ ብሄ/አስ ም/አስተዳዳሪ እና ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሀላፊ አይተነው ታዴ እና የአባይ ባንክ የእንጅባራ ቅርንጫፍ ስራአስኪያጅ ዘውድነህ አዲሱ በፈረሙት ስምምነት መሰረትም በዚህ አንድ አመት 100 የመንግስት ሰራተኞች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።

አቶ አይተነው እንደገለጹት የመግባቢያ ስምምነቱ ለአመታት መንግሥት ሰራተኛው ሲያቀርበው ለነበረውን ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው።የብድር አቅርቦቱ ከመንግስት ስራው ጎን ለጎን ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።ከስምምነቱ በኋላ በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ ያስገነዘቡት አቶ አይተነው ቀጣይ በመንግስት ሰራተኛው አንገብጋቢ ነገሮች ላይ የብድር አቅርቦቱ እንዲያመቻችም አሳስበዋል ።

በብድሩ ቅድሚያ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከዚህ ቀደም ብድር የሌለባቸው እና ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟሉት የብሄረሰብ አስተዳደሩ መንግስት ሰራተኞች መሆናቸውም ተገልጿል።

በስምምነቱ መሰረትም ባንኩ ለቤት እና መኪና መግዣ 95 በመቶ ብድሩን ያመቻቻል።ሌላኛው ቦታ ኑሯቸው የቤት መስሪያ የሚሆን ገንዘብ በብድር የቀረበ ሲሆን ፤ለ5 አመት የሚቆይ ደግሞ እስከ 500ሽህ ብር ለቤት ቁሳቁስ ማሟያ ብድር እንደሚሰጥ ታውቋል።

የብድር አመላለሱም በዝቅተኛ የወለድ መጠን(7 ፕርሰንት)እንዲሁም እስከ 25 አመት የሚቆይ መሆኑም ተመላክቷል።

የአባይ ባንክ የእንጅባራ ቅርንጫፍ ስራአስኪያጅ ዘውድነህ አዲሱ ፥ባንኩ ከዚህ ቀደም በሌሎች አካባቢዎች ለሰራተኞች የማበደር ልምድ ያለው ሲሆን ቀጣይ የመንግስት ሰራተኛውን የኢኮኖሚ ክፍተት ለመሙላት በሌሎች የብድር አማራጮች ጭምር ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

የመንግስት ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት አባይ ባንክ ከሌሎች አቻ ባንኮች ቀድሞ ለሰራተኛው የብድር አቅርቦት ማመቻቸቱ የእኛ ባንክ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ሰራተኛው በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን በሌሎች የብድር አቅርቦትም እንዲመጣ ጠይቀዋል ።

በዚህ አመት 100 የመንግስት ሰራተኞች የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱም ታውቋል።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.