የግሎባል ፒስ ባንክ ፣ የአፍሪካን ሬኔይሳንስ (Arts) ቴሌቪዥን እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሦስትዮሽ ሥምምነት
ጉርብትናን እናስቀድም በሚል መርህ ትውልድ ላይ በጋራ እንሥራ እንዲሁም ሠላምን ለማምጣት ወዳጅነቶችን በስፋት እንገንባ ብሎ የተነሳው ግሎባል ፒስ ባንክ ከአፍሪካን ሬኔይሳንስ(Arts) ቴሊቪዥን እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን በአገራዊ ጥቅማቸው የጎላ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የሦስትዮሽ ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በተከናወነበት መድረክ ላይ የሦስቱም ተቋማት መሪዎች እና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የአርትስ ቴሌቭዥን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል በላይነህ፣ የግሎባል ፒስ ባንክ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አርጋው አየለ እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሶሻል ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምርምር ተባባሪ ዲን የሆኑት ቢኒያም ሞረዳ (ዶ/ር) ተገኝተዋል ።
የግሎባል ፒስ ባንክ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አርጋው አየለ በበኩላቸው የሠላም ማጣት ያልጎዳው ሰው የለም ያሉ ሲሆን ተቋማቸው ሠላምን ለማጽናት በርካታ ሥራዎችን ላለፉት 18 ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን በመግለፅ የጋራ ስምምነቱ በአብሮነት ለመስራት ያግዛል ብለዋል።
የአርትስ ቴሌቭዥን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንዔል በላይነህ ከሁለቱ ተቋማት ጋር ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መልኩ ሲሠሩ መቆየታቸውን ገልጸው፣ ይህ ሥምምነት ከዚህ ቀደም የተሠሩ ሥራዎችን ይበልጥ እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል ።
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሶሻል ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምርምር ተባባሪ ዲን የሆኑት ቢኒያም ሞረዳ እንደዚህ አይነት የሶስትዮሽ ስምምነት በተለይ ደግሞ ለዩኒቨርስቲው ጠቃሚ እንደሆነና ዩኒቨርሲቲው ዋና ዓላማው ከመማር ማስተማሩ ባለፈ በምርምር እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ መስራት መሆኑን ገልጸዋል ።

6 months ago