በኢትዮጵያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚደረጉ የምርጫ አይነቶች እና ምንነታቸው
የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና
የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/11
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037,0983337690
መግቢያ #ethiopia | በኢትዮጵያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚደረጉ የምርጫ ስረአቶች ስንት አይነት እንዳሉ እና ምንነታቸው
የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና
የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/11እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 1133/11 አንጻር
አጠር ባለ መልኩ አቅርብናል።
1.. የምርጫ ዓይነቶች
በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የምርጫ ዓይነቶች የሚከተሉት
ናቸው፤
ሀ/ ጠቅላላ ምርጫ/General election/
ለ/ የአካባቢ ምርጫ/Local election/
ሐ/ ማሟያ ምርጫ/By_election/
መ/ ድጋሚ ምርጫ/Re_election/
ሠ/ ህዝበ ውሳኔ፡፡ /Referendum/
2. ጠቅላላ ምርጫ
ጠቅላላ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡ በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ ሆኖም ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ
ሲያገኘው እና ጉዳዩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውሳኔ ሲያገኝ በተለያየ ጊዜ እንዲካሄድ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ለኢ.ፌ.ደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከአንድ የምርጫ ክልል አንድ ተወካይ ብቻ ይመረጣል፡፡ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ቁጥር በየክልሉ ህግ መሠረት የሚወሰን ሆኖ ከአንድ የምርጫ ክልል
ከአንድ ተወካይ በላይ ለክልል ምክር ቤቶች አባልነት ሊመረጥ የሚችልበት የምርጫ ስረአት አይነት ነው።
3. የአካባቢ ምርጫ
የአካባቢ ምርጫ በህግ በተደነገገው መሠረት በየደረጃው የሚካሄድ የብሔረሰብ ዞን፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ ወይም የቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ነው፡፡
የአካባቢ ምርጫ ከአንድ ምርጫ ክልል በየደረጃው ለምክር ቤቶቹ የሚመረጡት ተወካዮች ቁጥር እያንዳንዱ ክልል በሚያወጣው ሕግ የሚወሰን ነው።
4. የማሟያ ምርጫ
የማሟያ ምርጫ የሚካሄደው በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በተለያየ ምክንያት የተጓደሉባቸው አባላት እንዲሟሉላቸው
ለቦርዱ ጥያቄ ሲያቀርቡ፤ ወይም ተፈጻሚነት ባለው ህግ መሠረት የቀረበ የይውረድልን ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው፡፡
5. ድጋሚ ምርጫ
ድጋሚ ምርጫ ከሚከተሉት ምክንያቶች
በአንዱ ሊካሄድ ይችላል ቦርዱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት
የምርጫ ውጤት እንዲሰረዝና ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ሲወስን ወይም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀረበለት አቤቱታ ላይ ተመስርቶ የምርጫ መደገም ውጤትን የሚያስከትል ውሳኔ ሲወስን የሚፈጸም የምርጫ አይነት ነው።
6.. ህዝበ ውሳኔ
ቦርዱ በህገ መንግሥቱ ወይም በሌሎች ህጎች መሠረት አግባብ ባለው አካል ሲወሰን የህዝብን ፍላጎት ለመለካት ወይም ለመወሰን ድምጽ እንዲሰጥ ህዝበ ውሳኔ የሚሰጥበት የምርጫ
አይነት ነው።
7. ማጠቃለያ
እነዚህ ምርጫዎች እንደ አስፈላጊነታቸው በኢፊድሪ ህገመንግስት፥በአዋጅ ቁጥር 1133/11 ፥ በአዋጅ ቁጥር 1162/11 እንዲሁም አግባብነት ባላቸው ህግች የሚፈጸሙ ሲሆን ይህ ጽሁፍ ለግንዛቤ ያህል የቀረበ ነው።
https://www.facebook.com

6 months ago