የሰይፉ ደግነቶች ጊዜ ጠብቀው እየፈነዱ ነው
በተመስገን ባዲሶ
#ethiopia | ሰው ደካማ ገመናውን እና ነውሩን ሸፍኖ በሚኖርበት ዓለም ሰይፉ ደግነቱን ደብቆ የኖረ ሰው ነው። አንዳንዴ የረሳቸው ውለታዎች ተመልሶ ከሰው ሲሰማቸው እንደ-አዲስ አብሮ ይደመማል። ሰጥቶ መርሳት ልማዱ ነው። ብዙ የደግነት አሻራዎቹን የት እና መቼ እንዳኖራቸው ዘንግቷቸዋል። ደግነት መደበኛ ሕይወቱ ስለሆነ በየጊዜው ያደርገዋል። እነዚህ ደግ የዋለባቸው ገጠመኞች ከዘመን ርቀት ጋር የሚዘነጉ ክምችቶች ይሆናሉ። ግን ውለታ የተዋለለት ሰው መቼም አይረሳቸውም። እንዴት ይረሳቸዋል? በአደባባይ አያወሩት ነገር የሰይፉ ውለታ እና ቃል አስሮ በዝምታ ሸብቦ ያኖራቸዋል።
👉....………ከሰይፉ የሕይወት-መርሕ ውስጥ አንዱ የሚያግዘው ሰው በፍፁም ሚስጥር-ጠባቂ መሆን አለበት። ሲያደርግ አደራው ይከብዳል። ወንጀሌን ደብቁልኝ የሚል እንጂ፣ ደግነቴ አይወራ የሚል አይመስልም። እንደ- እኔ ዓይነት ያገኘውን ለሰዎች የሚያካፍል ሰውን እንኳን በዝምታ ሸብቦኝ ኖሯል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ከህመሜ ጎን ሆኖ ያላገዘኝ ነገር የለም። ለዘመን መለወጫ ቤት ድረስ መጥቶ ለአውድ-ዓመት ብሎ 100 ሺ ብር ጀባ ሲለኝ እምብዛም ያልተገረምኩት እጆቹ አመላቸውን ስለማውቀው ነው። ደጋግሜ የእጁን-ጣዕም ስለቀመስኩት ሰበር-ዜና አልሆነብኝም። አደባባይ ወጥቼ ለሕክምና አግዙኝ ሳልል እስካሁን በነፃነት የታመምኩትና-ራሴን ያስታመምኩት የእነ-ሰይፉ ዓይነት ደግ እጆች ከጀርባ ምርኩዜ ስለሆኑ ነው። ሁሌ ጤናዬ ያሳስበዋል። በደወለ ቁጥር ……… ከእግዚአብሔር ሰላምታ ቀጥሎ ከአንደበቱ የሚወጣ ቃል ነው።
👉....……አሁን አሁን በተገኘው አጋጣሚ እንደ-Timeing Bomb ደግነቱ እየፈነዳ ነው። ሰዎችም ይኼ ድፍረት ሆኗቸው ደብቀው ያኖሩትን የውለታ ሚስጥር እያፈነዱት ነው። ያለፈው ሰኞ ለሰይፉ ተዘጋጅቶ በነበረው የአቀባበልና-የምሥጋና ፕሮግራም ላይ ከዕድምተኞች መሀል እንድካፈል በክብር ተጠርቼ ነበር። ግን ከጀግናው አትሌት ዋሚ-ቢራቱ ልደት ጋር ሰዓቱ ገጠመብኝና ሁለት ቦታ መከሰት አልቻልኩም። የዝግጅቱን አጠቃላይ ድባብ ግን በቴሌቭዥን መስኮት ቤቴ ሆኜ ተከታተልኩ ጥቂቶች ይኼን ምሥክርነት ሰጡ………
.
.
.
.
.
.
.....
«የሰይፉ ውለታ ብዙ አለብኝ። ከአስር ዓመት በፊት ቀብድ ከፍሎ፣ 'የቀረውን ክፈል!' ብሎ መኖሪያ ቤት እንዲኖረኝ ያደረገው ሰይፉ ነው፡፡» ሲል ድምጻዊ ታደለ ሮባ ደግነቱን መሰከረ።
👉....……ታዴ መድረክ እና አጋጣሚውን አግኝቶ አስር ዓመት ደብቆ የኖረውን የደግነቱን ሚስጥር አፈነዳው። ስለሰይፉ ደግነት በአደራ-ቃሉ የተለጎሙ አንደበቶች በየቦታው፣ በየቤቱ፣ በየሀገሩ ታፍነው አሉ። ውለታው በልባቸው የታሰረ ሺዎች አሉ። ስለሰይፉ ደግነት ለማውራት መድረኩን ቢያገኙ ከጉሊት ነጋዴ፣ ስኬትን እስከጨበጡ ሚሊየነሮች የሚያፈነዱት ውለታ አለባቸው። የሚገርመኝ ሰይፉ እነዚህን ደግነቶቹን የት እንደቀበራቸው አያስታውሰውም። ጊዜ ጠብቀው ሲፈነዱ ድምፁ ለጆሮው እንግዳ ይሆንበታል። እሱ ግን ጋዜጣ እንዲጀምር በአንድ ወቅት ያገዘውን የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት የአቶ አማረ አረጋዊን ውለታ ባ'ገኘው አጋጣሚ ያፈነዳዋል።
👉....……… ናቸው። እነሱ የቀበሩትን ደግነት እየዘነጉ፣ የተደረገላቸውን ግን መቼም አይረሱም። የሰው መጥፎም-ጥሩም ሥራ እንደ-አደራ ይቀመጣል። አንድ ባልታይዘር የተባለ ሴት-አውል አፍሪካዊ 400 የወሲብ ቅሌቶቹ በአንድ አዳር ፈንድተው አይደል ነውሩ ፀሐይ የሞቀው? የነውሩ ክምችት ግን የዘመናት ሥራው ውጤት ነው። ሰው ከሰራው ውጪ ምንም ታሪክ የለውም……በሰማይም-በምድርም ሰው በሥራው ይመዘናል። ሰይፉ ከምናውቀው የውጪ ማንነቱ ጀርባ ኽንዲህ ዓይነት ከባድ-ሚዛን የሆነ የደግነት ቆንጆ ነው። ሳይታይ በየቦታው የቀበራቸው ደግነቶች አሁን አሁን በየቦታው ጊዜ ጠብቀው እየፈነዱ ነው። ሰይፍሻ እኔም ታፍኜ ልሞት ነው………ላፈንዳው እንዴ?😃😃😃😃😃😃😃😃😃😃
ረጅም ዕድሜና-የተሟላ ጤና………ከእነ-መላው ቤተሰብህ ይስጥህ፣ ከፍ በልልን…………
/ሻሎም/

11 months ago