Logo
Getu Temesgen
ዩናይትድ እና የ415 ቀናት ጎፈሬ
#ethiopia | ኤድሪሴ ጋና ከኦልድትራፎርድ ጨርቁን ጥሎ ከዓለም ፊት አበደ ። የእራሱ የቡድን አጋሩ ኪንን በጥፊ ተማቶ ገና በጨዋታው ጅማሮ 13ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተባረረ ።

የሴኔጋላዊው ዕብደት ዩናይትድን የበለጠ ይረዳል ሲባል በቀይ ካርድ ተጨዋች የወጣበት ግን ማንቸስተር መሠለ ።

ኤቨርተን 1ለ0 ዩናይትድን እየመራ ከ80 ደቂቃ በላይ በ10 ተጨዋች ዘለቀ ።

ቶፊሶቹ የተጨዋች ብልጫ አድቫንቴጅ የተወሰደባቸው ሳይመስሉ በነፃነት በጀግንነት ለድል ተንቀሳቀሱ ። በላቀ ትኩረት እና ህብረትም እስከመጨረሻው ተዋደቁ ። በመጨረሻም ቶፊሶች አድናቆት የሚቸረው የአሸናፊነት ውጤትን ከእራሳቸው ጭምር ሊጋጠም ወደ ሜዳ የገባ የሚመስለው ኤድሪሴ ጋና ወፈፌነትን ጭምር ችለው ዩናይትድን ድል ነሱ ።

ባለፉት 5 ጨዋታዎችም ሳይሸነፍ ከመጓዙ ውጭ የረባ የቡድን የተደረጃ የሚታይ የጨዋታ እንቅስቃሴ ጥንካሬ ያልነበረው የአሞሪም ዩናይትድ ከጨዋታ ቀመር ሀሳቡ ጋር መግበባት ያልቻለ ሲባክን ያመሸ ጥራት የጎደለው ለዘብተኛ ቡድኑን እንደ ልማዱ አሳየ ።

ማንቸስተር ዩናይትድም በቀድሞዎ አሰልጣኙ ዴቭድ ሞየስ ተሸነፈ። ድሉ ከ13 ዓመት በፊት ዩናይትድን እንዲያሰለጥኑ በፈርጊ ተመርጠው መከራው ላይ ገና በጠዋት ተቀምጠው ጉድ ለሆኑት ዴቭድ ሞየስ ለመጀመሪያ ግዜ የተመዘገበ ነው።

ለዩናይትድ ውለታ ሊፈፅም ሜዳ የገባ የመሠለው የኢድሪሴ ጋና በመንደር ጨዋታ ዕንኳ የቀረው የለየለት ዕብደት የፈጠረለትን ክፍተት ሳይጠቀም ማንቸስተር ዩናይትድ ግራ ቀኝ እንደተራወጣ ሰሞናዊው የተሻለ የውጤት ጉዞውን ረስቶ ወደ ኖረበት ሽንፈቱም ተመልሷል ።

ከ80 ደቂቃ በላይ በቀይ ካርድ ተጨዋች የወጣበት ኤቨርተን ሳይሆን ዩናይትድ መስሎም ከኦልድትራፎርድ ታየ ።

ኤቨርተን በተሟላ ስኳዱ ከዩናይትድ ቢጫወት ምን ሊያሳየን ነበር ? ይህ ዩናይትድ ከሰሞኑ በማሸነፍ ውስጥ ሸፍኖት ያቆየውን ሰፊ የቡድን ድክመቱን በአግባቡ ያጋለጠ ጨዋታ ሆኖ ተጠኗቋል ።

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 12ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

⏰ ተጠናቀቀ

ማን ዩናይትድ 0-1 ኤቨርተን
ዴውስበሪሆል 29'⚽️

የ415 ቀናት ጎፈሬ፤
የእግር ኳስ ሕይወቱን እንዳጎፈረ ቀጠለ ...

Tribune sport

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.