ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነት ልትሰርዝ ይገባታል 👉 ባለሙያዎች
#ethiopia | ታህሳስ 3/1993 በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተፈረመው የአልጀርስ ስምምነት ባለ 6 አንቀጽ ሰነድ ሲሆን 4 መሰረታዊ ግቦች እንዳሉት ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን ባከበረ መንገድ እየተጎጓዘ ቢሆንም ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጠረች ያለው ተፅዕኖ ስምምነቱን ማቋረጥ የሚያስችል ነው የሚሉት የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂና ሴኩሪቲ ተንታኝ ያፌት መኮነን አሁን ላይ ኢትዮጵያ የአልጀርስ ስምምነትን ማቋረጥ ይጠበቅባታል ብለዋል፡፡
አስቀድሞ ስምምነቱ ላይ ክፍተት እንደነበር በማንሳት እንዲሁም ኤርትራም የሥምምነቱን አካል በግልጽ እየጣሰች በመሆኑ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱን በመሰረዝ ወደ ድርድር መሄድ እንደሚገባ አቶ ያፌት ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ አስቀድሞም ችግር ያለበት እንደነበር የሚያክሉት የአለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ዶክተር ግደይ ደገፋ፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይሁን የኤርትራ መንግስት ስምምነቱን አላከበሩም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ውዝግቦች በብሄራዊ ጥቅም አተረጓጎምና የስልጣን ጥቅም ትርጉም ላይ ከፍተኛ የግንዛቤ ችግር በመኖሩ እንደሆነ ያነሱት ባለሙያው፤ ስምምነቱን ከማፍረስ ይልቅ በአለም አቀፍ ህጉ ችግሮቹን ለመፍታት መሞከር ይሻላል ይላሉ።
አለም አቀፍ የሕግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ መንግስት ለስምምነቱ ተገዢ መሆን እንደሚገባው ነው የተናገሩት፡፡
ስምምነቱ አስቀድሞ ጥናት ሊደረግበት ይገባ እንደነበር ያነሱት ባለሙያው፤ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ስምምነቱን አላከብርም ካለች የአለም አቀፍ ድንበር ኮሚሽን የሰጠውን የድበር ላይ ውሳኔን አላከብርም እንደማለት የሚቆጠር በመሆኑ ስምምነቱን መሰረዝ እንደማትችልና በሃገሪቱ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖም ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል።
የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂና ሴኩሪቲ ተንታኝ ያፌት መኮንን ግን፤ ኤርትራ አለም አቀፍ የድንበር ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የወሰነውን እና የአልጀርሱ ስምምነት አካል የሆነውን ህግ ቀድማ በመጣስ የኢትዮጵያን ግዛት በመቆጣጠሯ፤ ኢትዮጵያ ስምምነቱን ብታፈርስ ተጠያቂ አያደርጋትም ባይ ናቸው ሲል መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

6 months ago