Logo
SeledaPost
ለጥንቃቄ በባምባሲ ከተማ ለቅርጫ ስጋነት ከተዘጋጀ ከብት ላይ ያጋጠመው ክስተት
‎
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ከተማ ‎ባለፈው ሀሙስ ማለትም ህዳር 11/2018 ዓ/ም  አንድ በሬ ከጎረቤት ቀሽማንዶ ገበያ ለቅርጫ የተገዛ ሲሆን በዕለቱ ለማረድ ወደ ባምባሲ ከተማ አስተዳደር ቄራ አገልግሎት በመሄድ ቅድመ ምርመራ ተደርጓል።
‎
‎በሬውም ዉጫዊ ምርመራ ያለፈ በመሆኑ ይታረድ እና የዉስጣዊ ምርመራ ደግሞ ሲደረግ የአጥንት ቲቢ በሽተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
‎
‎በዚህ የተነሳ የባምባሲ ከተማ አስተዳደር ቄራ አገልግሎት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዩኑስ አብዱረህማን በሬው ለምግብነት እንደማያገለግልና መቀበር እንዳለበት መወሰኑን ተናግረዋል።
‎
‎አቶ ዩኑስ ስጋዉ በአጥንት ቲቢ የተበከለ እና ለምግብነት የማያገለግል በመሆኑ እንዲሁም በከተማው ህዝብ ላይ የጤና ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አራጆችን አስተባብረው ሙሉ በሙሉ መቀበሩን ለባምባሲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት መልዕክት እንዲተላለፍ አሳውቀዋል።
‎
‎እንስሳቶች ጤነኛ መስለው በሰዉ ልጆች ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር ሊያስከትሉ በሚችሉ በሽታዎች የሚጠቁበት አጋጣሚዎች ሰፊ መሆኑን ባለሙያው አብራርተዋል።
‎
‎ስለሆነም መላው የወረዳችንና የከተማችን ማህበረሰቦች  ለሰርግ ፣ ለበዓል ፣ ለቅርጫ እና ለሉካንዳ ቤቶች እርድ የሚዘጋጁ ማንኛውም እንስሳት በሰዉ ልጆች ጤና ላይ ችግር እንዳያደርሱ በባለሙያ መመርመር እንደሚገባም አሳስበዋል።

seledadotio
seledadotio
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.