Logo
Getu Temesgen
44ቱ ቅዱስ ሚካኤል ጎንደር !
#ethiopia | በሰርክ የፈጣሪ ስም ይጠራባታል፣ ኪዳን ይደረስባታል፣ ቅዳሴ ይቀደስባታል፣ ምስጋና እና ውዳሴ ይቀርብባታል፣ ጸሎትና ምስጋና አይቋረጥባትም፣ ጠቢባን፣ ዘማሪያን፣ ጀግኖች፣ ነጋዴዎችና ሌሎች በአንድ ላይ የኖሩባት፣ የሚኖሩባት ታላቅ ከተማ ናት፡፡

አሁን በ19ነኛው አጋማሽ ጎንደር የጎብኙ ፈረንሳዊ ፍርቱና ጋሊነሪይ የአፍሪካ ፓሪስ በማለት የገለፁት በዘመኑ ከጎንደር በአስብ በኩል የሚደረገውን ንግድ ድመራ የነበረው መራቱ የተባለ አርመናዊ በካይሮ ባስፈረው መዛግብቱ ጎንደርን የኢስታንቡልን አራት እጥፍ ትልቅ የሆነች ከካይሮ ቀጥላ የዓለማችን ሁለተኛ ግዙፍ እንደ ነበረች በመሰከረላት የመናገሻዋ ከተማ ጎንደር መሐል ፒያሳ ነኝ ።

የዛሬዉ ከታሪክ ገፃችን መዳረሻዬ የሀገሬው ሰው አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ሲል የሚጠራው የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ነዉ !! ምናልባት ከአሁን በፊት ያልሰማችሁት 13ኛዉ የፋሲል ግብረ ህንፃዎች መግቢና ሌሎችንም ልንቃኝ ነዉና ተከተሉኝ ።

ከአፄ ፍሲል አብያተ መንግስት ግቢ ዙሪያውን ከሚገኙት ግምጃ ቤት ማርያም፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣አቡነ ተክለሀይማኖት፣አቡነ ሀራ ድንግል፣ባለ ወልድ እና እድሜ ጠገቡ ይሄውን የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ይጠቀሳሉ ።

ደብሩም አድባር ሰገድ በሚል የንግስና ስማቸው የሚታወቁት አፄ ዳዊት ወይም ዘማሪዉ ዳዊት በ1708 ዓ.ም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት በመሆን በትረ ስልጣኑን መያዛቸውን ተከትሎ በአማረ ጥበብ እንደተገነባ ድርሳናቱ ይገልፃሉ ።

ቆይ ለመሆኑ አፄ ዳዊት ማን ናቸዉ ? አትሉኝም ?

የድሮ ነገሥታት የክብራቸው ልክ የሚገለጥባት የዘመኑ ስልጡን መሀንዲሶችን የጥበብ ልህቀት ማስመስከሪያዋ
ጎብኚዎች ለማየት የሚመኟት አይተው በፍቅሯ የሚነደፉላት በናፍቆት የሚንሰፈስፉላት ሙሽሪት ጎንደር የመናገሻ መዲናነት ዘመን ከነገሱ ሃያላን ነገስታቶቿ መካከልም አንዱ ነበሩ ።

ለኪነጥበብ ልዩ ፍቅር እንደነበራቸው የሚነገርላቸው በገና ደርዳሪዉ ዳዊት ወይም በንግስና ስማቸዉ አድባር ሰገድ ዳዊት እንደሌሎቹ ነገስታት ዘመናቸውን ዋጅተው በጥበብ እና በሞገስ እስከዚህ ትውልድ የተንሰላሰለ አሻራ አስቀምጠው አልፈዋል ።

አድባር ሰገድ በሚል የንግስና ስማቸው የሚታወቁት አፄ ዳዊት ወይም ዘማሪዉ ዳዊት በዘመናቸዉ ከፈፀሟቸዉ ከሚጠቀሱ ተግባራት መካከልም በሃገራችን የመጀመርያው የሆነዉ በፋሲል አብያተ መንግስት ግቢ ዉስጥ ያስገነቡት እጅግ የሚያስደንቅ ቤተ ተዉኔትን ትያትር ቤት ፣ ከአፄ ፋሲል ግቢ ዙርያ ከሚገኙ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት አንዱ የሆነው ሃገሬዉ አጣጣሚ ሚካኤል እያለ የሚጠራው የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፣ በነገስታቱ ግቢ ዉስጥ የሚገኙት ደንበኛ የአንበሳ ቤቶች ዋነኞቹ ናቸዉ።

የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
ንጉሰ ነገሥቱ በዘመኑ ከግብጽ አሌክሳንደርያ በመጡት የኢትዮጵያ ጳጳስ አቡነ ክርስቶደሉ ባላባቱና ም ዕመናኑ በተገኙበት ሰኔ 1 ቀን 1709 የተመረቀ ሲሆን በአራት ማዕዘን ቅርጽ የተሰራው ይህ ቤተክርስቲያን ግድግዳው በጥቁር ድንጋይና ተቃትሎ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት በውሃ ተዘፍዝፎ በተብላላ ኖራ በጌጠኛ አሰራር እንደተገነባ አመታትን ተሻግሮ ዛሬም ድረስ ያልደበዘዘዉ ዉበቱ መረዳት ይቻላል ።

ደጀሰላሙ እና ከቤተ መንግስት ጋር ትይዩ የተሰራዉ ይህ ደብር በወቅቱ በሮቹ ከቁስቋም ተጠርቦ በመጣ ቀይ ልዝብ ድንጋይ በቅስት እንደተጌጠ ጣራው በባኅላዊ በተጠረበ እንጨት ወራጅ ተሰክተው ጠፍጣፋ ድንጋይ ከለበሰ በኋላ ውሃ እንዳይሰርግ በኖራ ተለብጦ በግድግዳው ላይ ወራጅ አሸንዳዎች ተደረጎበት እንደነበር ከመዛግብት ያገኘኋቸው መረጃዎች ይገልፃሉ ።

ከቤተ መንግስቱ ጋር "አስቄት" በር በተባለችና ከአስራ ሁለቱ የአፄ ፋሲል ግቢ በሮች በማይጠቀሰው በር በኩል ንጉሱ ነገሥቱና ባለሟሎቻቸው ይገቡ እንደነበር የታሪክ ባለሙያዎች ይናገራሉ ።

በአፀዱ ተሻግረዉ ወደ ታላቁ የመናገሻ ስፍራ ፋሲል አብያተ መንግስታት ሲያቀኑም በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግስት የተገነባው ትያትር ቤት እና የአንበሶች ቤት ይገኛሉ ።

ንጉሱ ለስነጥበብ እጅግ የተሰጡ በመሆናቸው በመጀመርያው የስልጣን ዘመናቸው በፋሲል አብያተ መንግስት ግቢ ዉስጥ እጅግ የሚያስደንቅ ቤተ ተዉኔትን አስገንብተዋል ።

ፀሀፈ ተዉኔት አያልነህ ሙላቱ ቲያትር ወደ ኢትዮጵያ መቼ እንደገባ ሲያስረዱ ብልጭታዉ በዛጉየ ስርዎ መንግስት እንደታየ በመጠቆም ነገር ግን ለዘመናዊ ቲያትር መመስረት በዋናነት የምትጠቀሰው ጎንደር ከተማ ስለመሆኗ ሲያስረዱ ይህንን አፄ ዳዊት ያስገነቡትን ቤተ ተዉኔት በመጥቀስ ነዉ ።

በገና የሚደረድሩት አፄ ዳዊት ሲበዛ ጥበብን አፍቃሪ እንደነበሩ የነገስታቱ ዜና መዋል ከትቦት እናገኘዋለን ።

በዘመናቸው ለሊቃውንት በተለይም ለክፍለ ዩሃንስ ከፍ ያለ ክብር እንደነበራቸው ቅኔዎቹ በመዝገብ ላይ እንዲሰፍሩና ከትዉልድ ወደትዉልድ እንዲነገር አድርገዋል ።

እኒህ ንጉሥ በፋሲል ግቢ ዉስጥ ያስገነቡት "ደባል" የሚባለው ቤተ ተዉኔት በወቅቱ የተለያዩ የጥበብ ስራዎች ይቀርቡበት የነበረ ሲሆን ህንፃዉ ዛሬም በግቢው ይገኛል ።

ታዴ የማመይ ልጅ
______

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.