ዶናልድ ትራምፕ ለእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ የ2,000 ዶላር ክፍያ እንደሚሰጥ አስታወቁ
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ እያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ በውጭ ዕቃዎች ላይ ከሚሰበሰበው ቀረጥ ገንዘብ ቢያንስ 2,000 ዶላር “ዲቪደንድ” እንደሚያገኝ አስታውቀዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ መድረካቸው “ትሩዝ ሶሻል” ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ “ቀረጥን የሚቃወሙ ሞኞች ናቸው። አሁን በዓለም ላይ እጅግ ባለጸጋ፣ እጅግ የተከበረች ሀገር ነው ያለን። ምንም አይነት የዋጋ ግሽበት የለብንም ማለት ይቻላል፣ የአክሲዮን ገበያው ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ላይ ከፍ ያለ ሲሆን፣ የሰዎች ቁጠባም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለዋል።
ትራምፕ አክለውም፣ “ትሪሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ገቢ እየሰበሰብን ነው፣ እናም በቅርቡ የአሜሪካን ግዙፍ የ37 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ መክፈል እንጀምራለን።
በመላ አገሪቱ አዳዲስ ፋብሪካዎችና ማምረቻ ተቋማት እየተገነቡ ነው፣ እንዲሁም ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች እየተደረጉ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።
እርሳቸው እንዳሉት፣ እያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ ከውጭ ዕቃዎች ቀረጥ በሚመጣው ገቢ ቢያንስ 2,000 ዶላር “ዲቪደንድ” በቅርቡ ይሰጠዋል። ነገር ግን ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ከዚህ ጥቅም ውጪ ይሆናሉ።
የአፈጻጸም ግልጽነት ማጣት
የአሜሪካው ግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሳንት በኤቢሲ ) “ዚስ ዊክ” በተሰኘው ፕሮግራም የትራምፕን ማስታወቂያ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ከመሠረታዊ ዓላማው አንጻር በመንግስት በኩል ከቀረጥ የሚገኘው ገቢ ቢጨምርም፣ ዋናው ግብ ገቢ መሰብሰብ ሳይሆን ማምረቻውን ወደ አሜሪካ መመለስ እና የንግድ ሚዛኑን ማስተካከል እንደሆነ ተናግረዋል።
ሆኖም፣ ትራምፕ ያወጁት የ2,000 ዶላር ዲቪደንድ በተግባር እንዴት እንደሚተገበር ግልጽ የሆነ ሀሳብ የለም።
ቤሳንት፣ “እስካሁን ከፕሬዚደንቱ ጋር ስለ ጉዳዩ አላወራሁም። ነገር ግን ይህ ዲቪደንድ እንደ የግብር ቅነሳ ወይም ከቀረጥ ነጻ ማድረግ ባሉ የተለያዩ መንገዶች ወደ ዜጎች ሊደርስ ይችላል” ብለዋል።
እንዲሁም፣ የፕሬዚደንቱ የግብር እቅድ በአገልግሎት ክፍያ እና በትርፍ ሰዓት ክፍያዎች ላይ ያለውን ታክስ ማስቀረት የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም የገንዘብ ጥቅሞችን ሊያስገኝ እንደሚችል ጠቁመዋል።
seledadotio

7 months ago