አውራጃዊነትን እየሰበኩ መዲናን መናፈቅ ሁለት የፖለቲካው ተቃርኖ...
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ )
#ethiopia እንግዲህ ከዝምታ እና ከረጅም ጊዜ ንባብ እንዲሁም ከነባራዊ እውነታ የተረዳሁትን እኔም ሳይረፍድብኝ በ37 ዓመቴ በእርግጥ ምንም እንዳልሰራሁ ይሰማኛል፤በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ሳላደርገው፤ሳልጽፈው እንዲሁም ሳልናገረው ብዬ በውስጤ ከሚቀርና የመገለጥ መንገድ (Emancipation)በጥልቅ ሲገባኝ በተለያየ ጊዜ እየፃፍኩ ያስቀመጥኳቸውን ቁርጥራጭ ማስተዋሻ እና ነገረ-ሀሳቦችን አካፍላለሁ።በአንድ ወቅት ስለነገሮች ሳጤን ይህ ነገር ከዓመታት በኃላ ታወሰኝ(Regional Integration in Africa)የሚለውን የሁለተኛ ዲግሪ የማስተርስ ትምህርት ኮርስ ስንወስድ በእርግጥ ውጤቱ "A" በማምጣት ቢጠናቀቅም ለአፍሪካ ውህደትና አንድነት ዋነኛው እክል (Regionalism) እንደሆነ የአንድ ወቅት መምህሪ የጋምቤላው ተወላጅ እና አመለ ሸጋው ዶ/ር ዲቪድ ሩች በክፍል ውስጥ አስተምረውናል፤በዚያም በወቅቱ ከእኔ ጋር ሲማሩ ከነበሩ ተማሪዎች ጋር ሰፊ ክርክር እና (Article Review) በማድረግ ወረቀት እናቀርብ ነበር።መቼም ወዳጆቼ አሁን የሶስተኛ ዲግሪውን(PhD) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማጠናቀቅ ላይ ያለው ትንታጉ የክፍላችን ሰቃይ እና ሀሳብ አፍላቂ የእዬብዘር ዘመዴ እና ሌሎች ንዋይ አለምአየሁ፣አብዲ፣ ኢሳያስ እና ብሩንዲያዊው አሌክስ... የክፍላችን ተማሪዎች ዋና የውይይት መሪዎች በመሆናቸው አይረሱትም።እኔም አውራጃዊነት ከብሔራዊ ጥቅም አኳያ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ድስኩር( Political Discourse) ውስጥ ለመመልከት ሞከርኩ ይህ ምልከታዬ (Empirical Approach ) ስነ-ዘዴ ይከተላል ።
"አውራጃዊነትን እየሰበኩ መዲናን መናፈቅ" ይላል (Preaching Provincialism while Coveting the Metropolis) የሚለውን የእንግሊዘኛ ሀረግ መጠቀሙ ተገቢ ይመስለኛል።ይህ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ የሚታየውን ውስብስብና ተቃራኒ ባህሪ የሚገልጽ ነው።ይህ ሁኔታ የሚያመለክተው አንዳንድ የፖለቲካ ልሂቃንና "አንቂዎች" ማንን እንደሚያነቁት እስካሁን አልገባኝም፤በአንድ በኩል ለጠባብ የክልል (አውራጃዊነት፤ጎጠኝነት) ጥቅም፣ማንነትና መለያየት በቆራጥነት ሲከራከሩ፣በሌላ በኩል ደግሞ የሀገርን ማዕከላዊ ሥልጣን፣ሀብትና ተፅዕኖ የፖለቲካ ተክለ-ስብዓና (A Political Personality Cult) ለማግኘት የሚደረገውን የጋለ ትግል ሲደግፉ እናስተውላለን፤ጉዳዮችን በሰከነ አዕምሮ ነገረ-ሀሳቡን ስንመረምረው እንዲህ ሆኖ እናገኘዋለን ።
የተቃርኖው ምንጭ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ፣ሁለት ዛፍ አይወጣም እንዲል ብሂሉ ፖለቲካው ሁለት መንታ መንገድ እንዲሆን እና ይህ የአስተሳሰብና የድርጊት መለያየት የመጣው ከሚከተሉት የፖለቲካ እውነታዎች ነው :-
🔴ማንነትና ሀብት፣ሲያሻኝ በማንኪያ ሲያሻኝ በእጄ:-አውራጃዊነት፣ጎጠኝነት የሚሰብኩ ኃይሎች መሠረታዊ የፖለቲካ ካፒታላቸውን (A Narrow view of Political theory) የሚገነቡት በክልልና በጠባብ ማንነት ላይ ነው።በእውቀት እና በብቃት አያምኑም፤ ኃይላቸውን የሚመዙት በዚህ መሰረት ነው። ሆኖም የፖለቲካ ሥልጣን የመጨረሻ ግብ የሚሆነው የሀገርን የሥልጣን፣ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ማዕከላዊነት መቆጣጠር ነው።
🔴የማዕከል መሪነትን መውሰድ እና እኔ ሁሉንም ካልባረኩት የሚል አስተሳሰብ:-ምንም እንኳን አንድ ክልል በራስ የመወሰን መብት በጽንሰ ሀሳብ ቢደገፍም፣ሀገሪቱ የመጨረሻ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት፣ የኢንቨስትመንት ፍሰት፣ የቢሮክራሲ ቁልፍ ቦታዎችና የዓለም አቀፍ ተሰሚነት ተፅዕኖ ከክልላዊ ሥልጣን እጅግ የላቀ በመሆኑ ያልተማከለ ሀይልን (Decentralization) አይፈልጉትም ቃላቸው እና ስብከቱ ሌላ ነው ።
🔴የቃልና የተግባር አለመጣጣም ፣በአንድ አፍ ሁለት ምላስ:-የፖለቲካ ልሂቃኑ በቃል ለክልላቸው ጥቅም ሲቆሙ፣በተግባር ግን ትልቁን ድርሻ የሚሰጡት ወደ ማዕከሉ በሚወስደው የሥልጣን ትግል ላይ ነው።የክልል የፖለቲካ ኃይል የሚለካው በመዲናው ላይ ባለው ተፅዕኖ ልክ ነው ብለው ያምናሉ ይህን ለማሳካት ደግሞ ሀገር እና ብሔራዊ ጥቅም፣ህዝብ ለነሱ ቦታ የለውም አሁንም ነዶ ሀሳብ ይዞው እንደ ቦይ ውሃ መጓዝን መርጠዋል ።ይህም መዲናን በመናፈቅ (Coveting the Metropolis) እና ትግል ብለው የሚስቡት ከግል ጥቅምና ዝና ብቻ ነው ይህ ማለት ደግሞ ታማኝነትታቸው ለግልና ለግል ነው። (Loyal to the Individuals not the State)
🔴በሀገር ግንባታ ላይ ያለው ተፅዕኖ (The Impact of Regionalism on Nation building):-
ይህ ተቃራኒ አሰላለፍ ለኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ ሂደት ትልቅ እንቅፋትና አደጋ አለው፤የአለመተማመን መፍጠር ጎጠኛ ኃይሎች በሁለት የተለያዩ መልዕክቶች (በክልል ለተከታዮቻቸው የጠባብ ማንነት እና በማዕከል ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሰፊ አንድነት) የሚወክሉ በመምሰል፣በመናገር፣በሕዝቡና በፖለቲካው ሂደት ላይ ያለውን እምነት ይሸረሽራሉ።
✍️እንደ መውጫ ⁉️
"አውራጃዊነትን( Regionalism)እየሰበኩ መዲናን መናፈቅ" የሚያሳየው የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ በስሜት እና "በበልሃ ልበልሃ "ስለሚመራ ነው ይህም ቂም በቀለኝነት እና በተራዘመ ጊዜ ግጭትና የሰላም ሚዛንን ያዛባል።ይህ ፖለቲካ መለያየት የዘላቂ እና የትውልድን ጥቅም እንዲሁም ሀገረ-መንግቱን ይጓዳል።በድስቱ ውስጥ ያለውን የጫው መጠን ለማወቅ አንዳንዶቹ ሲያሻቸው "በማንኪያ እንዳንዶቹ በእጃቸው " የአነባብሮ ፖለቲካ ስልት ይጠቀማሉ።ለዚህም የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የወደብ አቅርቦት ጥያቄን ሲንኳስሱት እንመለከታለን ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፀሃፊውን የኤክስ(X)ገፅ ይከተሉ:-
🔗 https://x.com/HDebasu?t=3H...

7 months ago