የጽሑፍ ወይም የሰነድ ማስረጃዎች በፍ/ር ክርክር መቼ ይቀርባሉ?
የኢትዮጵያ ፍ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 145
ፋንታሁን ደለለው ጠበቃና የህግ አማካሪ 0929101037/0983337690
መግቢያ #ethiopia | የማስረጃ አቀራረብ በተመለከተ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 137 ጀምሮ እንዴት መቅረብ እንዳለበት እስከ 146 ድረስ ተደንግጎ የተቀመጠ ቢሆንም በዚህ ህግ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 223 እንዲሁም 234 ላይ ተደንግጎ የተቀመጠ ሲሆን በዚህ ሕግ በሌሎች አንቀጾች ወይም ክፍሎች ተቀምጠዋል።
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነው ግን በፍ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 145 መሠረት የሚቀርቡ ማስረጃዎች በተመለከተ ነው።
1. በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 145 መሠረት የሚቀርቡ ማስረጃዎች በአንዳቸው ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ የጹህፍ ማስረጃ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ካመነበት በራሱ ስልጣን ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት ሲባል በትእዛዝ አስቀርቦ የሚመለከተው ማስረጃ ነው። ተከራካሪው ወገን በራሱ ስልጣን አቅም የጹህፍ ማስረጃውን አስቀርቦ በማስረጃነት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 223 መሠረት አስቀርቦ ለማያያዝ ያልቻለ እንደሆነ በፍርድ ቤቱ በኩል በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 145 መሠረት በማስረጃነት ተቆጥሮለት እንዲያያዝለት ሊጠይቅ ያስፈልጋል። ፍርድ ቤቱም በፍ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 231 መሰረት የክሱን ተቀባይነት ከተመለከተ በኋላ በ145 መሠረት እንዲቀርብለት የጠየቀውን ማስረጃ አስረጅነቱን ካመነበት በኀላ ተከሳሽ መልሱን ከማቅረቡ በፊት ፍርድ ቤቱ በትእዛዝ ማስረጃውን ካስቀረበ በኃላ ለተከሳሽ ከክሱ ጋር ደርሶት መልሱን ሊያቀርብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ተከሳሽ መልሱን ሲያቀርብ ከዚህ ማስረጃም ጭምር በመነሳት ነው።
አለበለዚያ ግን ይህ ማስረጃ የሚቀርበው ክስ ተሰምቶ ካለቀ በኋላ ለምርመራ ተቀጥሮ በሆነ ጊዜ ፍርድቤቱ በመጨረሻ ይህ ማስረጃ እንዲቀርብ የታዘዘ እንደሆነ ይህ ማስጃ በሚለው ላይ መልስ፣አስተያየት፣ ክርክር የመሥጠት እድሉ የሚታጣ ይሆናል። ይህ ሲሆን ተከራካሪዎች የመከራከራ መብት ከማጣታቸው በተጨማሪ የሚሰጠው ፍርድም ፍትሀዊነቱ ላይ ሚዛኑን ያጣል።
2. በተከሳሽ በኩሉም ይህ በማስረጃነት ተቆጥሮ እንደቀርብ ከተቆጠረም ፍርድቤት የክስ መስማት ሂደቱን ከመጀመሩ በፊት ይህንን በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 145 መረረት በማስረጃነት በማስቀረብ ለከሳሽ ደርሶት ለክስ መስማት ሂደቱ እንዲዘጋጁበት ማድረግ ያስፈልጋል።
3. ይህ ሂደት ከማስረጃ አቀራብ አላማ አንጻር ጭብጥ በመያዝ ተገቢውን ክርክር ለመያዝ ስለሚረዳ ነው። የፍ/ስ/ስ/ ህ ቁጥር 137 እንኳን የተመለከትነው እንደሆነ የሰነድ ወይም የጹህፍ ማስረጃ ከመጀመሪያ ቀነ ቀጠሮ ወይም በፊት መቅረብ እንዳለበት ያስቀምጣል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ተከራካሪ በፈለገበት ጊዜ ማስረጃ ቢያቀርብ አዲስ ጭብጥ ወይም ክርክር እየተነሳ የክስ መስማት ሂደቱ እንዳይበላሽ ነው።
4. ፍርድ ቤቱም ቢሆን በራሱ አነሳሽነት እንኳን ይህ ማስረጃ በ145 መሠረት እንዲቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥ እንኳን ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ቢሆን የተሻለ ነው። ይህ ቀደም ሲል እንደ ተገለጸው የክስ መስማቱ ሂደት የተንዛዛ እንዳይሆን አዲስ ማስረጃ በተፈጠረ ቁጥር አዲስ ክርክር አዲስ ጭብጥ በመያዝ የክርክሩ ሂደት እንዳይቀየር ነው። ጭብጥ ወይም ክርክር ከክስ መልስ ማስረጃ አንጻር ሊያዝ እንደሚቻል ከ246 _ 255 ድረስ ያሉትን የፍ/ስ/ስ/ህግ ድንጋጌዎችን መመልከት ይቻላል። ከእነዚህ ድንጋጌ አንጻር ጭብጥ የሚያዘው ከላይ እንዳስቀመጥነው ማስረጃ ለጭብጥ አያያዝ መሠረታዊ ምክንያት ያለው ሲሆን ለአቤቱታ መሻሻልም ምክንያት ሊኖረው ይችላል።
5. ማስረጃን በክርክር ውስጥ በተፈለገበት ጊዜ ሁሉ ማቅረብ እንደማይገባ ከላይ የተገለጹት ድንጋጌዎች የሚያስረዱ ሲሆን የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 256 ንም መመልከት የሚቻል ነው። በዚህም ድንጋጌ ከፍርድ በፊት ቀድሞ በስነስረአቱ አግባብ በጊዜው ለማቅረብ ከአቅም በላይ የሆነውን ማስረጃ እንደደተገኘ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ይህም ከአቤቱታው ጋር ወይም በመጀመሪያው ቀነ ቀጠሮ ወይም በፊት ማቅረብ ያልተቻለው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ማግኘት ያልተቻለ መሆኑን በማስረዳት ከፍርድ በፊት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 256 መሠረት ማቅረብ እንደሚቻል ተደንግጓል።
ይህ ማስረጃ ተቀባይነት ከተገኘ ፍርድ ቤቱ በነገሩ ላይ ለመስማት ቀጠሮ ይዞ ይሰማል።
6. ይህ አጠቃላይ የማስረጃ አቀራረብ ስነስርአት በክስ መስማት ሂደቱ ላይ ትልቅ ድርሻ ያለው ሲሆን ከጭብጥ አመሰራረት ጋር እንኳን ጉልህ ሚና አለው። የፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 249 ን እንኳን ስንመለከት ጭብጥ ለመመሥረት አስፈላጊ ሲሆን የሠነድ እና የሠው ማስረጃዎችን መመርመር አስፈላጊ የሚሆንበት ሁኔታ እንዳለ ያስቀምጣል።
7. ስለሆነም ክርክር ወደ ኋላ እንዳይመለስ በመለወጥ ወይም በማሻሻል የክስ መስማቱ ሂደት እንዳይጓተት ወይም ስህተት እንዳይፈጠር ማስረጃዎች በሙሉ በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 137 መሠረት ቢዘገይ በመጀመሪያ ቀነ ቀጠሮ ሊቀርቡ ወይም ከዚህ ቀጠሮ በፊት መቅረብ ያለባቸው ሲሆን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 145 በፍርድ ቤት በኩል ሊቀርቡ የሚገባቸው ማስረጃዎችም ለክርክሩ ሂደት አመቺነት ቀድሞ ክስ መስማት ከመጀመሩ በፊት አስቀድመው ሊቀርቡ የሚገቡ ናቸው።
Fantahun Delelew, lawyer, LLB,LL.M
https://t.me/Fantahunlawye...
https://www.facebook.com

9 months ago