በሶዶ እናቷ ገበያ መሄዷን ጠብቆ የ3 ዓመት ህጻንን የደፈረ ግለሰብ በ 17 ዓመት ጽኑ እሥራት ተቀጣ
ቴዎድሮስ ያዕቆብ የተባለ ይህ ግለሰብ በቀን 29/01/2018 ዓ.ም ዕለተ አርብ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ገደማ በሶዶ ከተማ ድል በጌሬራ ቀበሌ ቆንቶ መንደር አንዲት የ3 ዓመት ህፃን እናቷ ገበያ በሄደችበት አስገድዶ መድፈሩን የሶዶ ከተማ ፖሊስ ታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፔክተር ታመነች ባሳ ተነግረዋል ።
በመሆኑም ራሷን መከላከል በማትችል እና ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ በሚያስፈልጋት ህፃን ላይ አስቦ በፈፀመው የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል መከሰሱን የሴቶችና ህፃናት ልዩ ምርመራና ክስ ስራ ሂደት አስታውቋል።
ይህንን የወንጀል ጉዳይ ስያከራክር የቆየው የሶዶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ እና ህፃናት ምድብ ችሎት ዛሬ በቀን 26/02/2018 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ግለሰቡ ወንጀሉን መፈፀሙ በሰውና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛውን ለማስተማርና ሌሎችም ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ የሚያደርግ ነው ሲል ከሳሹ ለፖሊስ እጁን ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

7 months ago