ግለሰብ እና ብሔራዊ ጥቅም...
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | እውቁ የፖለቲካ ሳይንቲስት እና የአለምአቀፍ ግንኙነት ሊቃውንት ጆሴፍ ፍራንከል "International Relations in a Changing World " በሚለው መጽሐፉ እና በአጠቃላይ፣ይህ ርዕስ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ጥናት (International Relations) ትምህርት መስክ በሁሉም ህልዬቶች ከመጀመሪያው የንድፈ-ሀሳብ ትንተና "የብሔራዊ ጥቅምን (National Interest ) ጉዳይ በሚገባ ያስረዳል።
ብሔራዊ ጥቅም በአንድ ሉዓላዊ ሀገር መንግስት ዘላቂነት ባለው መልኩ ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው ዋና ዋና ግቦች፣ዓላማዎች እና ፍላጎቶች ድምር ውጤት ነው።እነዚህ ፍላጎቶች የሀገሪቱን ህልውና፣ደህንነት ፣ልማትና እና ብልጽግን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው።
ብሔራዊ ጥቅምን የሚወስኑት መሠረታዊ ነገሮች ደህንነት እና ሕልውና (Survival and Security) የግዛት ሉዓላዊነት እና አንድነት (Sovereignty and Territorial Integrity) የሀገሪቱን ድንበሮች ማስጠበቅ እና የውስጥ አስተዳደር በውጭ ጣልቃ ገብነት አለመወሰኑን ማረጋገጥ በጥብቅ መከታተል እና የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን የመከላከያ፣ደህነት ዘርፍን ማዘመን እና ዘመናዊነቱን ማጠናከርንም ይጨምራል።ይህ ሂደት የዜጎች ሰላም አስተማማኝነት የሀገሪቱን ዜጎች ከውስጥም ሆነ ከውጭ አደጋዎች መጠበቅ ያጠቃልላል ።
ብልጽግና እና ደኅንነት (Prosperity and Welfare) ኢኮኖሚያዊ ልማት፤የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ድህነትን መቀነስ፣ዘላቂና ሁሉን ያካተተ ዕድገት በተለያዩ ዘርፎች ማስመዝገብ እና በበቂ ሁኔታ የውጭ እና አለምአቀፍ ንግድ (Foreign Trade)ፍላጎቶችን ሚዛናዊነት በመጠበቅ ለሀገር ብሔራዊ ልማት ግቦች የሚረዱ የኢኮኖሚ ምንጮችንና መውጫዎችን ማረጋገጥ (እንደ ወደብና የትራንስፖርት መስመሮች፣የየብስ እና የአየር ትራንስፖርትን ይጨምራል)።
በተጨማሪም ክብርና እሴቶች (Prestige and Values) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገርን ክብርና ሞራል ከፍ ማድረግ ሲሆን በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉ እሴቶችንና መርሆችን ማስጠበቅ (እንደ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ዲሞክራሲ፣መልካም አስተዳደር ብልጽግና መሰል የታሪክ፣የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ማፅናት)ይሆናል።
እንደ መውጫ :-
በየትኛውም የአለም ክፍል የሚገኝ የሀገር እና ህዝብ የብሔራዊ ጥቅምን ጉዳይ በጋራና ትብብር በአንድነት ይሰራል።ይህ ማለት"የፖለቲካ ሀሳብ ልዩነት" (Political Differences) በግለሰቦች፣በቡድኖች ወይም በአካባቢዎች መካከል ባሉ የፖለቲካ እምነቶች፣አስተሳሰቦች (Ideologies) እና ስርዓቶች ውስጥ የሚታዩ ልዩነቶች ቢኖሩም የአገር ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ውስብስብ የሆነውን የፖለቲካ ልዩነት (Political Difference) እና የፖለቲካ አለመግባባት (Political Disagreement) ወደ ጎን በመተው ለዘላቂ ጥቅም ይሰራሉ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia

11 months ago