Logo
Getu Temesgen
“ አሁን“ የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ የሙዚቃ አልበም በድምቀት ተመረቀ

* (አልበሙ አርብ ጥቅምት 21 ይለቀቃል)

ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | የድምፃዊ ሐይሉ አመርጋ “ አሁን“ የተሰኝው አዲስ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአማራጭ የማሰቢያ ስፍራ በድምቀት ተመርቋል:: ድምፃዊ ሐይሉ የጃኖ ባንድ አባል ሲሆን በዚህ አልበም ላይ ወጣት የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት ምርጥ የግጥምና የዜማ ድርሰቶችን አካቶ በአዲሱ አልበሙ ላይ ይዞ ልን መጥቷል።

በአልበም ስራው ላይ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ አፈወርቅ፣ በረከት ተስፋአፅቂ፣ ኤርሚያስ ሞላ እና ኢብራሂም በቅንብር፣ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ እና ሮቤል ዳኜ በሚክሲንግና ማስሪንግ፣ ሀይሉ አመርጋ፣ አክሊሉ ገ/መድህንና ወንደሰን ይሁብ በግጥምና ዜማ ተሳትፈዋል፡፡

በዚህ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ላይ ከአዲሱ “ አሁነን “ አልበሙ ላይ የሙዚቃ ስራዎቹ በዲጄ የቀረቡ ሲሆን በተጭማሪ ድምጻዊ ሐይሉ አመርጋ የተመረጡ ስራዎቹን በፒያኖ ታጅቦ በድምፅ በአስገራሚ አቀራረብ ለታዳሚው አቅርቧል:: እንዲሁም ስለ ስራዎቹ ከታዳሚው አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የጃኞ ባንድ አባላትን ጨምሮ ድምፃዊያን የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል::

አልበሙ ውስጥ ካሉ ዘፈኖች ለሁለቱ የቪዲዮ ክሊፕ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን አልበሙ ከወጣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ እና ሶስት የሚሆኑ ዘፈኖቹ ደግሞ ገና እየተሰራላቸው እንደሚገኝ ድምጻዊው ገልጿል፡፡

አልበሙ ከጥቅምት 21 ጀምሮ በሀይሉ አመርጋ የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛል::

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.