"እንዳትሞቱ መስኮታችሁን ክፈቱ"
19 ሺህ ዜጎች በአመት
50 ዜጎች በየቀኑ በቲቢ በሽታ ይሞታሉ
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ19 ሺህ በላይ ዜጎች በቲቢ በሽታ ለህልፈት ይዳረጋሉ፦ ጤና ሚኒስቴር
በሀገራችን ኢትዮጵያ በየአመቱ በበሽታው የሚያዙ ዜጎችም ከ188 ሺህ በላይ መሆኑም ተነግሯል።
በመላው ኢትዮጵያ በበሽታው ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ ከ150 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህክምና ማዕከላት ገብተው ህክምናቸውን የሚከታተሉ ሲሆን ቀሪዎቹ በሽታው እንዳለባቸው ባለማወቃቸው ወደ ጤና ጣበያ አይመጡም ተብሏል።
በጤና ሚኒስቴር የቲቢ የስጋ ደዌና የሳንባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሀላፊ የሆኑት አቶ ታዬ ለታ እንደተናገሩት በሀገራችን በቲቢ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየአመቱ መቀነስ ቢያሳይም አሁንም ማህበረሰቡ ውስጥ ያለ በሽታ ነው ብለዋል።
የበሽታው መጠን ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ ከፍተኛ እንደሆነ የተናገሩት በሀገሪቱ 56 በመቶ የበሽታው ታማሚዎች ወንዶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንደዚሁም 10 በመቶ የሚሆኑ ታማማሚዎች ደግሞ ህጻናት እንደሆኑም ሀላፊው ነግረውናል።
በኢትዮጵያ በሽታው ከፍተኛ የሆነባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ታዬ በተለይም የማዕድን ማውጫ ቦታዎች በክልል ደረጃ ሲዳማና ኦሮሚያ የበሽታው መጠን ከፍተኛ የሚባል ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የቲቢ ጫና ለመቀነስ በዛሬው እለት ሀገራዊ የቲቢ በሽታ መከላከል ጥምረት ተመስርቷል።
የጤና ሚንስቴር ከላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከግሎባል ፈንድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የቲቢ በሽታን ከተቻለ ከሀገራችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ካልተቻለም በዜጎች ላይ እያደረሰው ያለውን የሞት እና ሌሎች ጉዳቶችን መቀነስ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚነኝ አሰልጣኝ አስታውቋል።
ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ትኩረት የተሰጠው በሀገራችን በቲቢ በሽታ መከላከል ላይ የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተካተቱበት የቲቢ በሽታ መካላከል ጥምረት ምስረታ በይፋ ተመስርቷል።
በአለም ላይ በአሁኑ ወቅት በገዳይነታቸው ከሚጠቀሱ በሽታዎች አንዱ የሆነው የቲቢ በሽታ እንደ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት በሀገራችን በገዳይነታቸው ቀዳሚ ከሆኑ በሽታዎች የቲቢ በሽታ እንዱ መሆኑን አረጋግጧል።
በሽታው በዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት መንግስትና ባለድርሻ አካላት በጋራ በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

11 months ago