ሰሜን ኮሪያ የተሳካ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
#ethiopia | ሰሜን ኮሪያ የተሳካ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች።
ሀገሪቱ ያደረገችው የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ እራሷን የመከላከል ቴክኒካል አቅሟን እያሳደገች ስለመሆኑ ግልጽ ማስረጃ መሆኑን አረጋግጣለች።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮሪያ በሚሳኤል አስተዳደር የተካሄደውን ሙከራ፣ የኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፀሃፊ ፓክ ጆንግ ቾን፣ የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ጃንግ ቻንግ ሃ መምራታቸውን የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አዲሱ የጦር መሣሪያ ስርዓት ከጠላት ሊሰነዘሩ የሚችሉ ስትራቴጂካዊ ጥቃቶችን በዘላቂነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመመከት እንደሚያስችል ተነግሯል።
የፒዮንግያንግ እንቅስቃሴ ጦርነትን ቀድሞ ለማስቀረት ያለመና ዓላማው ራስን መከላከል ብቻ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር ፒዮንግያንግ በርካታ የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ምስራቅ ባህር መተኮሷን አስታውቋል።
አሜሪካ ሙከራው ህገ-ወጥ እና የቀጠናውን መረጋጋት የሚረብሽ ነው በማለት ያወገዘች ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ የተለያዩ የሰላም ስምምነቶችን ከሚጥሱ ተጨማሪ ድርጊቶች እንዲትተቀብ ጠይቃለች።
በክብረአብ በላቸው #ጋዜጣፕላስ #ዓለምዓቀፍ #ሰሜንኮሪያ #ደቡብኮሪያ

8 months ago