ቻይና የማህበራዊ ሚደ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሰርተፍኬት እንዲኖራቸው እና የትምህርት ደረጃቸውን እንዲዘረዝሩ አስገደደች
የቻይና መንግሥት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨውን የሐሰት መረጃ ለመከላከል ቆራጥ እርምጃ እየወሰደ ነው። ከዚህ ወር ጀምሮ እንደ ሕክምና፣ ሕግ፣ ትምህርት እና ፋይናንስ ባሉ አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይዘት የሚፈጥሩ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በሚሸፍኑት መስክ የምስክር ወረቀት ወይም የይፋ ሥልጠና ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ይገደዳሉ።
ይህ ፖሊሲ የወጣው በሀገሪቱ የኢንተርኔት ደንብ ኃላፊነት ባለው በቻይና የሳይበር ምህዳር አስተዳደር ነው።
አዲሶቹ ሕጎች ይዘት ፈጣሪዎችን ብቻ ሳይሆን እንደ ዱዪን (የቲክ ቶክ የቻይና ስሪት)፣ ቢሊቢሊ እና ዌይቦ ያሉ ታላላቅ መድረኮችንም ይመለከታሉ፤ እነዚህም የተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ብቃትና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
እንደ Marketing4Ecommerce ዘገባ ከሆነ፣ በቻይና የሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶቻቸውን፣ ዲግሪዎቻቸውን ወይም ሌሎች የብቃት ማረጋገጫዎቻቸውን ለማቅረብ ሁለት ወራት ተሰጥቷቸዋል።
በተጨማሪም የመረጃዎቻቸውን ምንጭ በግልጽ የመጥቀስ እና በ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠሩ ወይም ድራማዊ አቀራረብ ያላቸውን ማንኛውንም ይዘቶች ምልክት የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
ይህ እርምጃ ግልጽነትን ለመጠበቅ እና በዲጂታል ዓለም ውስጥ የሚዘዋወረው ይዘት ሳይንሳዊ መሠረት እና ተዓማኒነት ያለው ተጠያቂነት እንዲኖረው ለማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ይታሰባል።

12 months ago