Logo
FastMereja
ሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ቀንን በደማቅ ሁኔታ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት አከበረ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ77ኛ ጊዜ "መተባበር ለበለፀገች ዓለም" በሚል መሪ ቃል የተከበረውን ይህን በዓል ሄኖሲስ ከአስራ አምስት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. አክብሯል። በዕለቱ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ሀብተየስ ዲሮ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ህብረት ስራ ማህበራት በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የላቀ ተሳትፎ ስላላቸው ይህንኑ ማስቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይህን በዓል አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የገንዘብ ቁጠባ እኛ ብድር ህብረት ስራ ማህበራት በጋራ እንዲያከብሩት የታቀደ በመሆኑ በአይሲኤ አፍሪካ ዕውቅና ተሰጥቶት ነበር። በዚህም ምክንያት የአይሲኤ አፍሪካ ጄኔራል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሮዝ ከሪሚ ከኬንያ በበይነ መረብ ባስተላለፉት መልዕክት እንዲህ ያሉ መድረኮች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳላቸው በመግለፅ አዘጋጆቹን አመስግነዋል ።

በእለቱ የፓናል ውይይት በሄኖሲስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አህፈሮም ገብረ አብ እንዲሁም ሌሎች ተጋባዦች የተካሄደ ሲሆን ፤ ኩነቱ በተጋባዦች መካከል የልምድ ልውውጥና የመተዋወቅ እድል የፈጠረ ሲሆን የእራት ግብዣ በመታደም ተጠናቋል።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.