Logo
YenetaTube
የአሜሪካ አዛዥ ናዛዥነት ከእንግዲህ አክትሟል ! /ኪም ጆንግ ኡን/

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊሞክረው ይችላል ብለው የሚያምኑትን አዲስ አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤልን በዛሬው እለት በፒዮንግያንግ አደባባዮች ማሳየታቸው ተነገረ ።

የኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ የተመሰረተበትን 80ኛ አመት በዓል ተከትሎ በፒዮንግያንግ አደባባይ በተዘጋጀው ትርኢት ሰሜን ኮሪያ የላቀውን Hwasong-20 አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤልን አሳይታለች ሲል የመንግስት ሚዲያ KCNA ዘግቧል።

አሁን ባሉት የአሜሪካ ሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶች ላይ ጭንቀትን ይጨምራሉ የተባለለትን አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ባሳዩበት ትልቅ ወታደራዊ ሰልፍ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ፣ የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ እና የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ መሪ ቶ ላም ተገኝተዋል ተብሏል ።

በሰልፉ ላይ ባደረጉት ንግግር ኪም በውጭ አገር ለሚያገለግሉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በተለይም በሩሲያ የዩክሬን ጦርነት ውስጥ “ሞቅ ያለ ማበረታቻ” አቅርበዋል፣ ጀግንነታቸው ከአገር መከላከያ አልፎ “ከሶሻሊስት ግንባታ” ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ መግለፃቸውን ኬሲኤንኤን ዘግቧል።

ሀገራቸው “ከአሜሪካ ኢምፔሪያሊስቶች እየተባባሰ የመጣውን የኒውክሌር ጦርነት ስጋት” ለመከላከል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልማቷን እና ኢኮኖሚዋን በአንድ ጊዜ እያራመደች ነው ብለዋል።

“ፓርቲያችን እና መንግስታችን አሁንም ጠንከር ያሉ ፖሊሲዎችን በመቀበል፣ ጠንካራ መርሆችን በማክበር እና ደፋር የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ የጠላቶቻችንን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ እርምጃዎችን እየታገለ ነው” ሲል ኪም ተናግሯል።

የላቀውን Hwasong-20 አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤልን KCNA የሀገሪቱ “ጠንካራው የኒውክሌር ስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያ ስርዓት” በማለት ገልጿል።

የHwasong ICBM ሰሜን ኮሪያ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የትኛውም ቦታ ላይ እንድትመታ ሊያስችላት ይችላል የተባለ ሲሆን
ለማረጋገጥ ግን ከዚህ አመት መጨረሻ በፊት ሲፈተሽ ለማየት መጠበቅ አለብን "በዩኤስ የተመሰረተው ካርኔጊ ኢንዶውመንት ለአለም አቀፍ ሰላም አንኪት ፓንዳ ተናግረዋል።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.