Logo
Getu Temesgen
ዓለማችን ድብርት በተያዙ ሰዎች ምክንያት ብዙ ሀብት ታጣለች ተባለ
#ethiopia | ይህን የሰማነው በስነ አዕምሮ ጉዳይ ላይ የሚሰራው ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል 34ኛ'ውን የዓለም አዕምሮ ጤና ቀን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው።

እንደ ጦርነት ያሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ለአዕምሮ ጤና መታወክ አንድ ሦስተኛ ያህል አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው የተባለው።

የህክምናው ሂድት ለአካላዊ ቁስለት እና ለለሌች የበሽታ አይነቶች ድጋፍ እንደሚሰጥ ሁሉ የአዕምሮ ጤና መታወክም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው ተብሏል።

አንድ ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ አደጋ የደረሰበት ሰው በ72 ሠአታት ውስጥ ባሉት ቀዳሚ ጊዜዎች ፈጣን የአዕምሮ ጤና ህክምና ካላገኘ ለተወሳሰበ የጤና ችግር ይጋለጣል ነው የተባለው።

በስነልቦና ድንገተኛ ህክምና (psychology First aid) እንደ ፆታዊ ጥቃት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ርዕደ-መሬት፣ መፈናቀል፣ ጦርነት፣ ድንገተኛ መርዶ እና ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ሲያጋጥሙ መከላከልና ምላሽ የመስጠት ህክምና ያስፈልጋል ተብሏል።

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.