Logo
YenetaTube
ከ24 ወራት ሰቀቀን ማጣት በኋላ የመኖር ተስፋችን ለምልማል ! /ፍልስጤማውያን /

ላለፉት አመታት የቦንብ ድምድምታ የመሳርያ እሩምታ ለአፍታ ተነጥሏት የማታዉቀዉ ጠባቧ የጋዛ ሰርጥ ፀጥ ረጭ ብላለች ።
ይህ የሆነው ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተኩስ አቁም እና የታገቱትን የመልቀቅ ስምምነት ካወጁ በኋላ ነዉ ።

ከሰዉ መኖሪያነት ወደ ሕዝብ ማለቂያነት፣ወደ አስከሬን መቀበሪያ-ፍርስራሽ መከመሪያነት በተቀየረችዉ ጋዛ ከዚህ ሁሉ መሀት በተአምር የተረፈችዉ የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ኤናስ ባራቃ ከሁለት አመታት በኋላ የመጣውን የሰላም ተስፋ, የመዳን ተስፋ ደስታ ነው. ስትል ትገልፃለች ።

ለቴሌግራፍ እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “ይህ ትልቅ ስኬት ነው፣ ለሁለት አመታት ከተካሄደው የቦምብ ፍንዳታ በኋላ ይህ ጦርነት ለአፍታም ቢሆን ይቆማል ብለን አልጠበቅንም ነበር። አሁን ስለ ልጆቼ ተረጋጋሁ እና ተስፋ ሞላኝ።

የደስታ እና የውጥረት ድብልቅ የታየባቸው እነዚህ የጋዛ ሰልፈኞች ሀሙስ- ጠዋት ላይ እስራኤል እና ሃማስ በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ እጅግ አጥፊ የሆነውን ጦርነት ለማቆም ስምምነት መፈራረማቸው የተኩስ አቁም ስምምነት ሐሙስ ምሽት ላይ ተግባራዊ ማድረጋቸውን ተከትሎ የታየ ነዉ ።

ዘገቦች እንዳመለከቱት ሁለት ዓመት በደፈነዉ ጦርነት እስራኤል ከ85ሺሕ ቶን በሚበልጥ ቦምብ ጋዛ ላይ ወድቋል ።

የሚሳዬል፣ ድሮን፣ መድፍ፣ አዳፍኔ፣ ጥይቱን ዉርጅብኝ በዝርዝር ያጠኑት አልነገሩንም።የጋዛ ከተማ-መንደሮች፣ ሆስፒታል-ትምሕርት ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት-መኖሪያ ቤቶች፣ ቤተ-እምነቶች ወድመዋል።

የፍልስጤም ባለሥልጣናት እንደሚሉት በትንሽ ግምት ከ70 ሺሕ በላይ ፍልስጤማዊ አልቋል።ከ170ሺሕ በላይ አካሉ ጎድሏል።እስራኤል ርዳታ እንዳይገባ በማገዷ ብቻ በረሐብ ከ400 በላይ ሰዉ ሞቷል።ከዚህ በኋላ ነዉ ሐሙስ ዕለት፣ የጋዛ ሲቪሎች፣ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የወደፊት ተስፋ እንዳላቸው መቀበል የጀመሩት ።

ባራካ ከቤቴ ሀኖን የምትባል ሰሜናዊ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ኦማር አል ቃታታ በአሁኑ ጊዜ በዋናነት ፍርስራሽ የሆነች እና የሃማስ ጦር በብዛት በሚገኝባት ግዛት በመኖሯ አሁንም የጦርነት ስጋትና ጥርጣሬዎች እንዳላት ያረጋገጠች ናት።

"በዚህ ስምምነት የቦምብ ጥቃቱን፣ መፈናቀሉን እና ስቃዩን ለማስቆም ደስተኞች ነን" ስትል ተናግራለች። "አምስት ልጆች አሉኝ እና እንደፈለጉት ምግብ እንደሌለ ልነግራቸው ሰልችቶኛል." ብላለች ።

ትላንት ምሽት የሰላሙ ስምምነት በአከባቢው ወሬው ሲሰራጭ፣ ሰዎች በጨለማ ውስጥ ተሰባስበው እየዘፈኑ ወይም በአቅራቢያው ያለውን ሰው በቴሌፎን በመደወል - ከ24 ወራት ጦርነት በኋላ፣ በህይወት መቆየታቸው ብስራት አብስረዋል ።

በተመሳሳይ በቴል አቪቭ የሆስቴጅስ አደባባይ የታየዉ፣ ስሜቱ የደስታ እና ጥልቅ እፎይታ ነበር።

በህይወት ካሉት 20 ታጋቾች አንዷ የሆነችው የማታን እናት ኢናቭ ዛንጋውከር፣ “ለማመን ይከብዳል፣ አፌ ደርቋል። እንባዎቼ መፍሰስ አያቆሙም። እንዴት መተንፈስ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም።” ስትል ተናግራለች ።

ሁለቱ ወንድ ልጆቿ ለወራት በጋዛ የታገቱባት ከኒር ኦዝ 12 የዜና ወኪል ፡ "ትራምፕን እና ሁሉንም አመሰግናለሁ። ማንንም ለማመስገን ምንም ቃላት የለኝም።አሁን ልጆቼን ስለ እቅፍ እና ስለ መሳም ብቻ ነው እያለምኩት፣ ያለሁት "
ከምስራቃዊ ካን ዮኒስ የመጣው ካማል ሻሃዳ ለዚች አፍታ ተስፋ በማድረግ ለሁለት አመታት ያህል በየቀኑ ሬዲዮን እንደከፈተ ተናግሯል።

“ትናንት ምሽት፣ ከሁለት አመታት ኃይለኛ የቦምብ ጥቃት በኋላ ምድር በደስታ ስትጨፍር ተሰማኝ” ብሏል።
ብዙ ጊዜ ተፈናቅለው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ግንኙነት ያቋረጡት የ57 አመቱ አዛውንት ።

"ወደ አካባቢዬ ተመልሼ ጎረቤቶቼን እና ቤተሰቤን ማግኘት እፈልጋለሁ" ሲል ተናግሯል። "በመፈናቀሉ እርስ በርስ ለያይቶናል, እና ስለማንኛውም ሰው ምንም የምናውቀው ነገር የለም.

"ይህ ስምምነት ከሞት እና ከውድመት አድኖናል፣ ከረሃብ ርቀን ወደ ህይወታችን በተሻለ መንገድ መመለስ እንፈልጋለን።"

ታዋቂው የጋዛ ጋዜጠኛ ሃዊዲ ሃምዛ እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “በመጨረሻም የጋዛን ጦርነት ለማስቆም በተደረሰው ስምምነት ዮሲ በእስራኤል ጎዳና ላይ እያከበሩ ነው።በጋዛው መሀሙድ እያከበረ ነው።ብሏል ።

እንደ ራፋህ ያሉ አካባቢዎች ከሁለት ዓመታት ግጭት በኋላ 'የድንጋይ ክምር' ቢሆኑም ጋዛውያን በደስታ ሲያከብሩ ታይተዋል ።

ወደ አካባቢው ስንመለስ፣ ከራፋ የመጣው ኢብራሂም ኦማር፣ “በውጭ አገር ህይወት መፈለግ እፈልጋለሁ፣ ጋዛ ሙሉ በሙሉ ወድማለች፣ ራፋህ የድንጋይ ክምር ብቻ ናት” በማለት ስለጠፋው የወደፊት ሃዘን ተናግሯል።

የ27 ዓመቱ ወጣት ከጦርነቱ በፊት አፓርታማ ለመግዛት እና ለማግባት የሚያስችል በቂ ገንዘብ አጠራቅሞ እንደነበረ ይናገራል ።

በጦርነቱ ምክንያት የነበረው ሁሉ እንዳልነበረ ሁኖበታል "በቂ ድካም እና ኪሳራ ደርሶብናል" ብሏል። "ይህ ለሁለት አመታት ጋዛ ነበር እና ስለ ህይወታችን እያለቀስን ነበር."አሁን ግን የመኖር ተስፋችን ለምልሟል ሲል ገልጿል ። እነዚህንና ሌሎች የሁለቱ ዓመቱ ጥፋት-ዉድመት፣ የመጨረሻ የሰላም ድርድር ስምምነት በኋላ የተሰሙ የደስታ ዜናዎች ናቸዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.