ሀብታም አገሮች ከድሆች በሚሰበስቡት የአየር ንብረት ፋይናንስ ብድር 42% ትርፍ እያገኙ ነው ተባለ
አየር ንብረት ፋይናንስ ዋነኛ ክፍል አሁን ባለው አሠራር ታዳጊ አገራት ላይ የዕዳ ጫናን ከማባባስ ባለፈ ለሀብታም አገራት ከፍተኛ ትርፍ እያስገኘ መሆኑን ኦክስፋም እና ኬር በጋራ ያወጡት ሪፖርት አመልክተዋል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው 65% የሚሆነው የአየር ንብረት ፋይናንስ የሚቀርበው በብድር መልክ ሲሆን፣ ታዳጊ አገራት ለሚቀበሉት $5 ዶላር ፋይናንስ $7 ዶላር መልሰው እየከፈሉ ነው።
ይህም ሀብታም አገራት "ቀውስን እንደ ትርፍ የመጠቀም" (crisis profiteering) አካሄድ ውስጥ መሆናቸውን ያሳያል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በተለይም ፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ጣሊያን ከፍተኛ ተጠያቂ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳሉ።
ሀብታም አገራት በ2022 ዓ.ም. $116 ቢሊዮን ማሰባሰባቸውን ቢናገሩም፣ ትክክለኛው እሴት ግን $28-35 ቢሊዮን ብቻ ነው ያለዉ ይህ ግኝት ከአየር ንብረት ፋይናንስ ወደ ሁለት ሦስተኛ የሚጠጋው በተለመደው የወለድ መጠን የሚሰጥ ብድር ነው ሲል አጋልጧል ።
በዚህም ምክንያት የብድር ተመላሽ ክፍያዎች ከሚሰጠው ገንዘብ በልጠው በ42% ትርፍ ለባለዕዳዎቹ አስገኝተዋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት እና አነስተኛ ደሴቶች ታዳጊ አገሮች ከጠቅላላው የፋይናንስ ድጋፍ በቅደም ተከተል 19.5% እና 2.9% ብቻ አግኝተዋል።
ሪፖርቱ ሀብታም አገራት ከ1960ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ የውጭ ዕርዳታ ቅነሳ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጿል። ይህም የአየር ንብረት ፋይናንስን የበለጠ ለመቀነስ ስጋት ሆኗል።
seledadotio

10 months ago