Logo
YenetaTube
በሊቀ ሰማዕታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘመን የነበሩና ሰማዕትነት የተቀበሉ፣ ከማዕድ በኋላ ስብሐት ተብሎ ስማቸው ተጠርቶ መጉረስ ሙታንን እንደሚያስምር ቃል ኪዳን የተሰጣቸው አባት ናቸው አባ ቡላ ወይም አቡነ አቢብ፡፡

በሃገራችን በኢትዮጵያ በስማቸው የታነጹ 3ት ታላላቅና ጥንታዊ ገዳማት አሏቸው፡፡ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ሲኸን፤ አቢብ ደግሞ የብዙዎች አባት፣ የመልካም ሥራ ኹሉ ባለቤት ማለት ነው፡፡ ገድላቸው የተከበረ አባት፣ በትሩፋት የተጋ፣ የመልካም ነገሮች ኹሉ አባት፣ ይላቸዋል፡፡ የተውለዱት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሮም ሉፊ በሚባል አውራጃ የካቲት 16 ነው፡፡ ወላጆቻቸው እጅግ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት ከመክስምያኖስ ሸሽተው በበረሃ ሳሉ በመልአክ ብሥራት ተወልደዋል፡፡

ሲጸነሱም ወላጆቻቸው የእግዚአብሔር መልአክ በሮማይስጥ ቋንቋ “ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው” የሚል የብርሃን ጽሑፍ በዛፍ ላይ ሲጽፍ ዐይተዋል:: ሕጻኑ ቡላ በዘመነ ሰማዕታት በመወለዱ ለአንድ ዓመት ሳይጠመቅ ቆይቶ እመቤታችን ለሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ወደ በረሃ ወርዶ እንዲያጠምቀው አዘዝችው፤ ሊያጠምቀው ሲል ሕፃኑ ተነስቶ እጆቹንም ዘርግቶ "አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡ የሕፃኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው፡፡ እነርሱም በዛፉ ላይ የተገለጸውን ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ:: ወላጆቹ ገና በ10 ዓመቱ ተከታትለው ስላረፉ ጎረቤቶች አሳድገውታል፡፡

ሃገረ ገዢው ለጣዖት ስገዱ ብሎ አዋጅ ባስነገረ ጊዜ በሕፃን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ፡፡ ሃገረ ገዢውም ተበሳጭቶ ስፍር ቁጥር የሌለው መከራና ስቃይ አበዛበት፡፡ ይሁንና ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከሞቶ አስነሳው፡፡ ቅዱስ ቡላ ወደ ሌላ ከሃዲ መኰንን ዘንድ ሄዶ ስለአምልኮ ጣዖቱ ገሠጸው፡፡ ያም ከሃዲ መኰንን ብዙ ካሠቃየው በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ለ2ኛ ጊዜ ከሰማይ ወርዶ ቅዱስ ቡላን ከሞት አስነሣው፡፡ ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ በምንኩስና እንዲኖር መታዘዙን ነገረው፡፡ አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዘወትር ዐርብ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን፣ የመድኀኔ ዓለምን ሕማማት እያሰበ ስጋውን በተለያየ መከራ እየጎዳ ኖሯል፡፡ ምንም ነገር ሳይቀምስ፤ መዝሙረ ዳዊትን እየጸለየ ለ42 ዓመታት ጹሟል፡፡

በአንዲት ቀንም ከረጅም ዛፍ ላይ ቁልቁል በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን በረታበትና ገደለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ተገልጦለት ከሞት አስነሣውና “ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ተባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህ” አለው፡፡ አቡነ አቢብ ታላቁ አባ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፍም ገዳሙ በመላእክት ተሞላ:: ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና “በእንተ አቡነ አቢብ” ስለ አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው የለመኑትን ልመና አምላካችን ተቀብሎላቸው ዛሬም በዚህ በቃል ኪዳናቸው የሚያስምሩ ሆነዋል፡፡

ገዳማውያን ዓለምን ትተዋልና ቃል ኪዳናቸው ምሕረትን ያስገኛል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.