የወጣቶች ኢንቨስትመንት ባንክ ሊቋቋም ነው
#ethiopia | የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልማት ባንክ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ማስፋፊያ ባገኘው ድጋፍ፣ የወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ኢንቨስትመንት ባንክ (Youth Entrepreneurs Investment Bank ) ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር መፈራረሙ ተገለጸ፡፡
ባንኩ ወጣቶች በሥራ ፈጠራ ስነ-ምህዳሩ ላይ የሚያጋጥሟቸውን የፋይናንስና የአቅም ክፍተት የሚሞላ ነው ያሉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ይህም መንግስት ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አክለውም፤ "የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ለወጣቶቻችን ተስፋ የሆነውን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ለሰጡት ጠንካራ አመራር እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ባንክ ላደረገው ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ" ብለዋል፡፡

10 months ago