*የአሜሪካ መንግስት የመዘጋቱ ነገር
#ethiopia | የአሜሪካ መንግስት ከትላንት ኦክቶበር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተዘግቷል። የመንግስት መዘጋት የሚከሰተው የአዲሱ የበጀት አመት ሳይገባ ሁለቱ የአሜሪካ ም/ቤቶች በፕሬዝዳንቱ በቀረበላቸው የበጀት ረቂቅ ላይ ተስማምተው ማጽደቅ ሳይችሉ ሲቀሩ ነው።
-የአሁኑ መዘጋት ለምን ተከሰተ?
በፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበው የአዲሱ የበጀት አመት ረቂቅ፣ ሪፐብሊካኖች በሚበዙበት በተወካዮች ም/ቢት (House) ጸድቆ ወደ እንደራሴወች ም/ቤት (Senate) ተመርቶ ነበር። ይሄንኑ ረቂቅ ለማጽደቅ የሚያስፈልገው ድምጽ 60 ነው። በም/ቢቱ ውስጥ ሪፑብሊካን 53፣ ዲሞክራቶች ደግሞ 47 ናቸው። ይሄንኑ በጀት ከደገፉ ሁለት ዲሞክራቶች በስተቀር 45 ዲሞክራቶች በጀቱ በተለምዶ የጤና መድህን ዋስትናን፣ የማህበራዊ ድጋፎችን፣ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰወች የሚሰጡ ድጎማወችን ይጎዳል በሚል ተቃውመውታል።
ሪፐብሊካኖችም የትራምፕን ‘ትልቅ ቆንጆ ህግ’ (Big Beautiful Bill) ምንም ሳይሸራረፍ ለማሳለፍ በእምቢታውቸው ጸንተዋል። እናም የድጋፍ ድምጹ 60 ስላልሞላ (55 ብቻ ድጋፍ ነው ያለው) ረቂቅ በጀቱ፤ ህግ ሳይሆን ቀርቷል። ለወትሮው ይሄ የፖለቲካ ልዩነት እስኪፈታ ድረስ ከሁለት ሳምንት እስከ 3 ወር ድረስ ሊዘልቅ የሚችል ጊዜያዊ በጀት (Stop Gap) ላይ መግባባት ላይ አልተደረሰም።
-መዘጋቱ ያለው ተጽዕኖ
መንግስት በመዘጋቱ 803 ሺ የፌደራል ሰራተኞች በጀት እስኪለቀቅ ድረስ ምንም ደሞዝ ሳይከፈላቸው ስራ አቁመው እቤታቸው እንዲቆዩ (furloughed) የተደረጉ ሲሆን ፣ ሌሎች 700 ሺ ሰራተኞች ደግሞ ሳይከፈላቸው ስራቸውን እንዲቀጥሉ ታዘዋል። እነዚህ ሰራተኞች በጀቱ ሲጸድቅ የሰሩበት ወደኋላ ታስቦ ይከፈላቸዋል።
-ታሪካዊ ዳራ
መንግስት በህግ አውጪወችና በፓርቲወች ፖለቲካዊ እሰጣ’ገባ ሳቢያ መዘጋቱ አዲስ አይደለም። ከ1980 ወዲህ 10 የሚሆኑ የመንግስት መዘጋቶች ተከስተዋል። ከነዚህ ውስጥ ረጅሙ በ2019 ዓ/ም፣ በዶናልድ ትራምፕ የመጀመርያ የስልጣን ዘመን ወቅት የተከሰተው ሲሆን ለ35 ቀናት ያህል ቆይቷል።
-ስራቸውን የሚቀጥሉት እነማን ናቸው?
የሚሊቴሪና የብሄራዊ ደህንነት ሰራተኞች፣ የህግ አስከባሪ አካላት፣ የአየር በረራ ደህን ነት ተቆጣጣሪወች፣ የአደጋ ምላሽ ሰጪወች፣ ፌደራል ሚሊቴሪ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያወች፣ ድምበር ጠባቂወች፣ የመንገድ ደህንነት ባልደረቦች እና ባጠቃላይ በፌደራል መንግስት ውስጥ አስፈላጊ (Essential) ተብለው የተመደቡ ሰራተኞች ስራቸውን አያስተጓጉሉም።
-በህዝቡ ላይ ያለው ጫና
የፓስፖርት እድሳት፣ የቪዛ መስጠት፣ የግብር አገልግሎቶች፣ የንግድ ፍቃድና ብድሮች ሁሉ በሚገባው ፍጥነት መተግበር አይችሉም። የፌደራል መንግስት ሰራተኛ ቤተሰቦች የእለት ተዕለት ህይወታቸው ከባድ ይሆናል፣ ህጉ ጸድቆ ደሞዝ ማግኘቱ እስኪቀጥል ድረስ የእለት አስቤዛ፣ የቤት ኪራይም ሆነ ሌሎች ወጪወችን መሸፈን ሊከብዳቸው ይችላል። ሱቆች፣ ሬስቶራንቶች፣ የቱሪስም መስህቦች፣ ቤተመዘክሮች እና ሌሎች ተቋማት ከወትሮው በተለየ ገቢያቸው ያሽቆልቁላል። የመንግስት መዘጋቱ ከቀናት አልፎ ሳምንታትን ካስቆጠረ ደግሞ የግብይት ኢኮኖሚው ላይ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።
በመንግስት መዘጋት ሳብያ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ቢቋረጥም የችግሩ ፈጣሪ የሆኑት የሁለቱም ም/ቤት አባላት ግን ደሞዛቸው አይቋረጥም። ፖለቲከኞች የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ጣት ሲጠቋቆሙ፣ ህዝቡና ኢኮኖሚው አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል።
#governmentshutdown #usa #dmv #ethiopia #followerseveryonehighlights
Abebe Feleke (አበበ ፈለቀ)

9 months ago