Logo
FastMereja
ያንጎ ኢትዮጵያ እና ጆኒ ራጋ ተፈራረሙ !!!
ያንጎ ኢትዮጵያ እና ጆኒ ራጋ "ውሃ እና እሳት" በተሰኘው አዲስ አልበም ሙዚቃን፣ ባህልን እና ማህበረሰብን ለማክበር አንድ ሆኑ !!!
…
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ መስከረም 21, 2018 - ያንጎ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ በታላቅ ዝግጅት ተመልሶ ከመጣው አንጋፋው የኢትዮጵያ ድምፃዊ ጆኒ ራጋ ጋር "ውሃ እና እሳት" በተሰኘው አዲስ አልበሙ ላይ አብሮ መስራቱን በኩራት ያስታውቃል። ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳጅ ከሆኑ ድምፃውያን መካከል የአንዱን መመለስ ከማክበሩም በተጨማሪ፣ ያንጎ የአገር ውስጥ ተሰጥኦዎችን እና የባህል መገለጫዎችን ለመደገፍ ያለውን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት ያሳያል።

በያንጎ የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ይቅናአለም አበበ ፕሮግራም ላይ ሲናገሩ፥ "የጆኒ ራጋ ሙዚቃ ሁሌም የኢትዮጵያን መንፈስ እና ነፍስ የሚወክል ነው። ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ በነበረው የድምፃዊው መመለስ ላይ ከእርሱ ጋር በመተባበራችን ትልቅ ክስተትን ከማክበር ባለፈ፣ ያንጎ የአገር ውስጥ ተሰጥኦዎች ማህበረሰብን በማነሳሳት፣ በማስተማር እና በማዋሀድ ባለው ኃይል ላይ ያለውን እምነት ዳግም እያረጋገጥን ነው። ይህ ትብብር ከመዝናኛ በላይ የሆነው ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ጥልቅ ግንኙነት እና ያንጎን የዕለት ተዕለት ሕይወታቸው አካል ላደረጉት አሽከርካሪዎቻችን፣ ደንበኞቻችን እና አድናቂዎቻችን ያለንን ክብር የሚያሳይ ነው" ብለዋል።

ጆኒ ራጋ በበኩሉ፥ "ከያንጎ ጋር ያለው ይህ ትብብር ስለ ዳግም መመለሴ አልበም ብቻ አይደለም፤ ፅናትን፣ ማህበረሰብን እና የኢትዮጵያን ሙዚቃ ጉዞን ስለማክበር ጭምር ነው። ላለፉት 20 ዓመታት፣ የኮንሰርት ጉብኝቶቺ እና የቀጥታ ስርጭት ትርኢቶች ወቅት ከጎኔ ለነበሩኝ ታማኝ አድናቂዎቼ ምስጋና ይገባቸዋል፤ በተለይም ለአርቲስቶች መብት እና በኢትዮጵያ የሮያሊቲ ክፍያ እንዲጀመር በምታገልበት ወቅት ከጎኔ ነበሩ። በ'ውሃ እና እሳት' አልበሜ፣ የተረጋጋ መንፈስን እና አስደሳች በዓላትን የሚተርኩ ታሪኮችን በማጋራት ለሙዚቃ ቤተሰቤ ውለታውን መመለስ እፈልጋለሁ። ከያንጎ ጋር መስራታችን ይህንን ራዕይ በየመንገዱ፣ በጉዟቸው እና በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውስጥ ላሉ ሰዎች ይበልጥ ለማቅረብ ያስችለናል። በጋራ፣ አልበም ብቻ እያወጣን አይደለም፤ የሁላችንም የሆነ የባህል ክስተት እየፈጠርን ነው" ብሏል።

በዚህ አጋርነት ያንጎ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን፣ አሽከርካሪዎችን እና ሰፊውን ማህበረሰብ የጆኒ ራጋን መመለስ በደስታ እንዲቀበሉ እና በ"ውሃ እና እሳት" አልበም እንዲዝናኑ ይጋብዛል። አድናቂዎች ከአልበሙ መውጣት ጋር ተያይዞ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን፣ ልዩ ይዘቶችን እና ልዩ ዝግጅቶችን ለማግኘት የጆኒ ራጋን የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ ትብብር በያንጎ እና በጆኒ ራጋ መካከል ለረጅም ጊዜ በቆየው ግንኙነት ላይ የተገነባ ነው። ከዚህ ቀደም አርቲስቱ አሽከርካሪዎችን ስለ መተግበሪያው አጠቃቀም በሚያስተምር ተወዳጅ ማስታወቂያ (ጂንግል) ላይ ከያንጎ ጋር ሰርቷል፤ ይህም ልዩ የሆነውን የሙዚቃ ስልቱን ከተግባራዊ መመሪያ ጋር አጣምሮ አቅርቧል። ያ ሽርክና ሙዚቃ ማህበረሰቦችን በማገናኘት እና የአሽከርካሪዎችን ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ ምን ያህል ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚችል አሳይቷል። ይህ ደግሞ ያንጎ ፈጠራን ከባህል ጋር በማዋሀድ አገልግሎቶቹ ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዲፈጥሩ እና ለኢትዮጵያ የፈጠራ ኢኮኖሚ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ያለውን ሰፊ ራዕይ ዳግም ያረጋግጣል።

ስለ ያንጎ ቡድን

ያንጎ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤቱን በዱባይ ያደረገ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙ ቴክኖሎጂዎችን ለአካባቢው ማኅበረሰቦች ተስማሚ በሆነ መልኩ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች የሚያቀርብ ኩባንያ ነው። ለፈጠራ ባለው ቁርጠኝነት፣ በአለም ዙሪያ ያሉ መሪ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተለያዩ ክልሎች እንከን የለሽ እና የተቀናጁ ዕለታዊ አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡ተልእኳችን በአለም ላይ ያሉ ፈጠራዎች እና በአካባቢ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ልዩነት ማቃለል፣ ግንኙነቶችን ማጎልበት እና የዕለት ተዕለት የኑሮ ልምዶችን ማጎልበት ነው። የያንጎ ባለብዙ-ተግባር መተግበሪያ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ ባሉ 25+ አገሮች ውስጥ በርካታ የዲጂታል ከተማ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የያንጎ ብዙ ባለ ብዙ ቋንቋ መተግበሪያ በአንድሮይድ እና አይ.ኦ.ኤስ iOS ላይ በነጻ ይገኛል።

###
For Immediate Release

Yango Ethiopia and Johnny Raga Unite to Celebrate Music, Culture, and Community with New Album Water and Fire

Addis Ababa, Ethiopia, 2 October, 2025 - Yango Ethiopia is proud to announce its collaboration with legendary Ethiopian singer Johnny Raga on his new album Water and Fire, marking his major comeback after 20 years. This partnership not only celebrates the return of one of Ethiopia’s most iconic voices but also underscores Yango’s ongoing commitment to supporting local talent and cultural expression.

Speaking on the collaboration, Dr. Yekenalem Abebe, Representative of Yango in Ethiopia said: “Johnny Raga’s music has always carried the spirit and soul of Ethiopia. By partnering with him on this long-awaited comeback, we are not only celebrating a cultural milestone but also reaffirming Yango’s belief in the power of local talent to inspire, educate, and unite communities. This collaboration is more than entertainment—it is a reflection of our deep connection to Ethiopia and our drivers, customers, and fans who make Yango part of their daily lives.”

Johnny Raga said: "This collaboration with Yango is more than just about my comeback album; it’s about celebrating resilience, community, and the journey of Ethiopian music. Over the past 20 years, I’ve been blessed with loyal fans who stood by me through tours and live performances, even as I fought for artists’ rights and the introduction of royalties in Ethiopia. With Water and Fire, I want to give back to my music family by sharing stories of calm reflection and fiery celebration. Partnering with Yango allows us to bring this vision closer to the people on the streets, in their rides, and in their daily lives. Together, we’re not just releasing an album; we’re creating a cultural moment that belongs to all of us."

Through this partnership, Yango invites music lovers, drivers, and the wider community to embrace Johnny Raga’s return and enjoy the album Water and Fire. Fans are encouraged to follow Johnny Raga’s channels for updates, exclusive content, and special features surrounding the release.

The collaboration builds on a long-standing relationship between Yango and Johnny Raga. Previously, the artist worked with Yango to produce a popular jingle that educated drivers on platform use, blending his unique sound with practical guidance. That partnership proved the powerful role music can play in connecting communities and advancing driver engagement. This also reaffirms Yango’s broader vision of blending innovation with culture, ensuring its services resonate deeply with local communities while contributing positively to Ethiopia’s creative economy.

About Yango

Yango Group is a global tech company headquartered in Dubai, transforming globally sourced technologies into everyday services that are tailored to local communities.Yango Ethiopia is operated by franchises G2G IT Solutions S.C and Elegance Import and Export PLC. With an unwavering commitment to innovation, we reshape and enhance leading cutting-edge technologies from around the world into seamlessly integrated daily services for diverse regions. Our mission is to bridge the gap between leading world innovations and local communities, fostering connections and enhancing everyday living experiences. Yango’s multi-functional app offers several digital city services across 25+ countries in Africa, Latin America, Europe, and the Middle East. Yango's multilingual app is available for free on Android and iOS.

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.