Logo
SeledaPost
በስዊድን 30,000 ሰዎች የዲጂታል ቁልፍ ማይክሮ ቺፕ በእጅ ጣታቸው አስተከሉ

በስዊድን ውስጥ ከ30,000 የሚበልጡ ሰዎች በፈቃደኝነት በእጃቸው ውስጥ የሩዝ ፍሬ የሚያህል ጥቃቅን ማይክሮ ቺፖች መትከላቸው ታውቋል።

ይህ ቴክኖሎጂ እንደ ዲጂታል ቁልፍ፣ የመክፈያ ዘዴ እና መታወቂያ በመሆን የዕለት ተዕለት ኑሮን ለማቀላጠፍ እየዋለ ይገኛል።

ቺፖቹ በሲሪንጅ እርዳታ በአውራ ጣትና በጣት መካከል በፍጥነት የሚተከሉ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች በሩን ለመክፈት፣ በባቡር ለመጓዝ፣ ለግሮሰሪ ለመክፈል እንዲሁም ወደ ስፖርት ማዕከል ለመግባት እጃቸውን ማንቀሳቀስ ብቻ በቂ ሆኖላቸዋል ነው የተባለው።

ተከታዮቹ የኪስ ቦርሳ እና ካርዶችን የመያዝ ግዴታን በማስቀረት የሚገኘውን ምቾት እንደ ትልቁ ጥቅሙ ይገልጻሉ።

ይሁን እንጂ የዚህ የቴክኖሎጂ አዝማሚያ መስፋፋት በብዙ ወገኖች ዘንድ ስለ ግላዊነት፣ ክትትል እና የሳይበር ደህንነት ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። ተቺዎች ቺፖቹ ሊጠለፉ (hacked) እና መረጃ አላግባብ ሊውል ይችላል የሚል ስጋት ሲያነሱ፣ ደጋፊዎቹ ግን ቺፑ ከውጪ መረጃ የማያስተላልፍ በመሆኑ ለከፍተኛ ክትትል አያጋልጥም በማለት ይከራከራሉ።

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.