Logo
FIDEL POST NEWS
" በአፍሪካ ቀንድ ፣ በቀይ ባህር ፣ በናይል ተፋሰስ ዙሪያ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ " - ኤርትራ

በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግሥታት (UN) ጉባኤ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ጋር እየመከሩ ነው።

ትላንትና ከኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ጋር ውይይት አደርገዋል።

ከትላንቱ ውይይት አንዱ #ኢትዮጵያ ወደ አደባባይ ይዛው የወጣችውና ዓለም አቀፍ አጀንዳ ያደረገችው የቀይ ባህር ጉዳይ ይገኝበታል።

የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ ሀገራቸው ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን በጠበቀ ሁኔታ በጋራ ጉዳዮች ላይ በተለም በአፍሪካ ቀንድ ፣ በናይል ተፋሰስ፣ #በቀይ_ባህር   ዙሪያ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች ተናግረዋል።

ኤርትራ ለቀጠናዊ ሰላምና ዘላቂ ልማት ቁርጠኛ መሆኗን የገለጹት ሳሌህ ከአሜሪካ ጋር ትብብር ለማድረግ የተፈጠረውን እድል ሀገራቸው በደስታ እንደምትቀበለ አመልክተዋል።

የአሜሪካው ከፍተኛ ባለስልጣን ማሳድ ቦሎስ  ሀገራቸው አሜሪካ ለዓለም አቀፍ ንግድ፣ ደህንነት እና ፀረ-ሽብርተኝነት ጥረቶች ወሳኝ በሆነ ቀጠና ውስጥ ውይይት እና መግባባትን ለመፍጠር ፅኑ ፍላጎት እንዳላት አስምረውበታል።

ውይይቱ በአሜሪካ እና ኤርትራ ግንኙነት ላይ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት መንገድ የሚጠርግ እንደሆነና ይህም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሠረተ ልማት፣ በትራንስፖርት፣ ግንኙነት እና ደህንነት አጋርነት ላይ ለውይይት በር ሊከፍት የሚችል እንደሆነ አመልክተዋል።

የቆዩ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።

ሁለቱም ወገኖች በሚቀጥሉት ወራት ግንኙነታቸው ለመቀጠል በመስማማት ውይይታቸውን ቋጭተዋል።

በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ከቀናት በፊት እዚህ #ኢትዮጵያ ነበሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትር በጽሕፈት ቤት ተገኝተውም ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደርገው ነው የሄዱት።

#ቀይ_ባህር #redsea

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#tikvahethiopiafamilyaa

tikvahethiopia
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.