Logo
YenetaTube
ለፍልስጥኤም እዉቅና መስጠት አይገባም !/ዶናልድ ትራምፕ/

የአለም አድራጊ ፈጣሪ ነኝ የምትለው አሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለፍልስጥኤም የሐገርነት እውቅና መስጠት ማለት ሽብርተኝነትን መደገፍ ማለት ነዉ ማለታቸው ተሰማ ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና
የሰጡ የአሜሪካ አጋሮች ባደረጉት ውሳኔ ደስተኛ አለመሆናቸውን እና በሃማስ ለተፈጸመው የሽብር ተግባር “ሽልማት” በማለት መዉቀሳቸዉ ተዘግቧል ።

ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በዩኤን ላይ ለአለም መሪዎች ባደረጉት ንግግር የፍልስጤም መንግስትን እዉቅና የሰጡ ሀገራት ሀማስ ኦክቶበር 7 ቀን 2023 በእስራኤል ላይ ለተፈፀመው ጥቃት “ሽልማት” እና ማበረታቻ ነዉ ሲሉ የሰሷቸው ሲሆን በሐማስ እስር ቤት የቀሩትን እስራኤላውያን ታጋቾችን ለመልቀቅ ቅድሚያ አልሰጡም ብለዋል ።

አክለዉም የአሜሪካ ወዳጅ የምዕራባውያን ሀገራት ለፍልስጤም መንግስት የሰጡትን እውቅና ውድቅ በማድረግ ሰላምን የሚደግፉ ሰዎች እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቅ አንድ መሆን አለባቸው ሲሉ ለ UNGA ተናግረዋል ።
" ለፍልስጤም መንግስት በአንድ ወገን እውቅና ለመስጠት ። የሃማስ አሸባሪዎች ለፈጸሙት ግፍ በጣም ትልቅ የሞራል ድጋፍ እንዲሁም ቀጣይ ግጭትን ለማበረታታት ያህል ነዉ " ብለዋል ትራምፕ።

ትራምፕ የተኩስ አቁም ድርድርን አለመሳካትም ጋዛን በሚያስተዳድረው ሃማስ ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን የፍልስጤም ቡድን "ሰላም ለመፍጠር ምክንያታዊ የሆኑ ስምምነቶችን በተደጋጋሚ ውድቅ አድርጓል" ሲሉ ተናግረዋል ።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸዉ በሁለቱ መንግስታት መፍትሄ ላይ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለፍልስጤማውያን መንግስት "መብት እንጂ ሽልማት አይደለም" ብለዋል.። ሲሉ

የዩናይትድ ኪንግደም እና የካናዳ ከፍተኛ ባለስልጣናት በእነዚያ ሀገራት የፍልስጤም ግዛትን በመቀበል ከትራምፕ አስተዳደር ትንሽ የግል ግፊትና ጫና እንዳለ ለPOLITICO የዜና ወኪል ተናግረዋል ።

ባለፈው ሳምንት የሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ለካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ዩናይትድ ኪንግደም መሪዎች የፍልስጤም መንግስት እውቅና መስጠት እንደ ምላሽ “የቅጣት እርምጃዎችን ሊጋብዝ ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሲል ያስነበበው አልጀዚራ ነዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.