Logo
SeledaPost
ዜዎታር በተሰኘ ኩባንያ ገንዘብ ተጭበርብረናል በሚል ደንበኞች ቅሬታን ቢያቀርቡም ኩባንያዉ ዝምታን መርጧል

ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸዉን የተናገሩ ግለሰቦች እንዳሉት አቶ አበበ ባይሌ የሻነዉ የሚባሉ ግለሰብን ጨምሮ ስድስት ሰዎች በርካታ ሰዎችን ህጋዊና መቀመጫዉን ዉጪ ሀገር ካደረገ ዜዎታር ከተባለ ኩባንያ ጋር እንደሚሰሩ ይናገራሉ፡፡ የበርካታ ወጣቶችን ህይወት መቀየር እንደሚፈልጉ በማሳመን ወደዚህ ኩባንያ ብር ስታስገቡ እጥፉን ታገኛላችሁ በማለት የማጭበርበር ተግባር ተፈጽሞብናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተደምጠዋል፡፡

እነዚህ ስድስት ግለሰቦች በየጊዜው የስብሰባ አዳራሾችን በመከራየት በርካታ ሰዎችን በመሠብሰብ እንዴት ወደዚህ ኩባንያ ብር አስገብተው ትርፋማ እንደሚሆኑ ስልጠና ይሰጣሉ ። ለጣቢያችን ቅሬታ ካቀረቡ ግለሰቦች መካከል አንዱ እንደተናገረዉ አቶ አበበ የሚባሉት ግለሰብ በተደጋጋሚ ስልክ እየደወሉ እና በአካል እያገኙኝ ኩባንያዉን ብቀላቀል ህይወቴ እንደሚሻሻል ቢነግሩኝም ስራዉ እንዳልገባኝ ለቴክኖሎጂ ያለኝም ቅርበት አናሳ መሆኑን ብነግራቸዉም በግድ አሳምነዉ ወደ ስራ ቀላቅለዉኛል ይላል ።

በራሳቸዉ ባይናንስ ገንዘቡን ገቢ እንደሚያደርጉ ትርፉን እንደሚሰጡኝ በመንገር 31ሺህ 500 ብር ገቢ ሳደርግ ሪዋርድ ተብሎ የተወሰነ ብር ሲሰጡኝ ነገሩ እዉነት መስሎኝ በድጋሚ 162ሺህ ብር ገቢ አድርጌ ትርፉን ስጠይቅ የተወሰነ ብር ከጨመርኩ ወዲያዉ እንደሚመለስልኝ ሲያሳምኑኝ ተጨማሪ ብር ባስገባም ምንም ትርፍ ሳላገኝ ከ200 ሺህ ብር በላይ ተጭበርበራለዉ ሲል አክሏል ። ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ እንዳለዉ የተወሰነ ብር እና 10 ሰዎችን በእኔ በኩል ሳመጣ ሽልማት 16ሺህ ብር ሲሰጡኝ ነገሩ ተስፋ ሰጪ መስሎኝ ከ300ሺህ ብር በላይ ተጭበርብራለዉ ብሏል ።

ብሩ ለምን እንደማይመለስላቸዉ በተደጋጋሚ አቶ አበበ ቢያወራቸዉም በሲስተም ችግር ነዉ ታገሱ ተብለዉ ለረጅም ጊዜ በእምነት ቢጠብቁም ዜዎታር የተሰኘዉ መተግበሪያ መዘጋቱን እና አቶ አበበንም ማግኘት እንዳልቻሉ አንስተዋል ።በቅሬታ አቅራቢዎቺ የማጭበርበር ተግባር ባሉት ድርጊት በርካታ ሰዎች ትዳራቸው መፍረሱን ፣ ለአእምሮ በሽታ የተጋለጡ መኖራቸዉ ይናገራሉል ። በዚህ የፒራሚድ ድርጊት ሌሎች ሰዎች እንዳትታለሉ ጥንቃቄ አድርጉ ያሉት ለጣቢያችን ቅሬታቸዉን ያቀረቡ ግለሰቦች የሚመለከተው የህግ አካል ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢዉ እርምጃ እንዲወሰድ ሌሎችንም ከዚህ የማጭበርበር ተግባር የመከላከል ስራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል ።

በጉዳዩ ዙሪያ ብስራት ሬዲዮ አቶ አበበን ለማነጋገር ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ ስልክ ሊነሳ ባለመቻሉ ምላሻቸዉን ማካተት አልቻልንም፡፡ ብስራት በዚህ ጉዳይ ማብራሪያና ምለሽ ለመስጠት ለሚፈልግ የኩባንያዉ አካል አሁንም ምላሻቸዉን ለማካተት ዝግጁ መሆኑን ያሳዉቃል፡፡

seledadotio
seledadotio
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.