Logo
Getu Temesgen
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ አቻ ተለያዩ
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ በዘጠነኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ሲቲ መሪ ሆኖ ነበር።

ይሁንና ተቀይሮ የገባው ጋብርኤል ማርቲኔሊ በ93ኛው ደቂቃ አርሰናል አቻ ያደረገችውን ወሳኝ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው አርሰናል የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደ ሲሆን የቆሙ ኳሶችን ተጠቅሞ ግብ ለማስቆጠር ጥረት ሲያደርግ ታይቷል።

ማንችስተር ሲቲ በመልሶ ማጥቃት የጨዋታ ስልት እና በፈጣን ሽግግር ወደ ተጋጣሚው የግብ ክልል በመድረስ ግብ የማስቆጠር ስትራቴጂን ተግብሯል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ10 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ማንችስተር ሲቲ በሰባት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ሰንደርላንድ እና አስቶንቪላ አንድ አቻ ሲለያዩ የቦርንማውዝ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.