Logo
FastMereja
ትችላለች🌼🌼🌼 300ሺህ ብር ሽልማት

የበሱፍቃድ ሪል እሴት ልማት ድርጅት ከምንጃር ሸንኮራ፣ አረርቲ ከተማ 300,000 ብር የማበረታቻ ሽልማት አብስሯል።

ሪል እስቴት ልማት ድርጅቱ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመሥራት አርዓያ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣቶች ችሎታቸውን እንዲያሳድጉና ሕልማቸውን እንዲኖሩ እየደገፈ ይገኛል።

አሁንም የፋና ላምሮት 5ኛው ዙር የአሸናፊዎች አሸናፊ ላይ በብርቱ ችሎታዋ በከፍተኛ ብቃቷ አሸናፊ ለሆነችው ከዚህ ቀደም ወደ አሸናፊዎች አሸናፊ ዙር በብቃት ባለፈችበት ወቅት 50,000 ሺህ ብር ማትጊያ ያበረከተው ድርጅቱ በድጋሜ ወጣት እየሩሳሌም አሰፋን ለማበረታታት የ300,000 ሺህ ብር ሽልማት ለማበርከት ቃል ገብቷል።

እናመሰግናለን🌼🌼🌼

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.