8 months ago
ኢትዮ ቴሌኮም የ“ቴሌስትሪም” የተሰኘ አገልግሎት አስተዋወቀ
#ethiopia | የኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠንና ዘመናዊ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር የሚያስችለውን “ቴሌስትሪም” (teleStream) የተሰኘ የይዘት ማስተላለፊያ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
አገልግሎቱ በፋይበርና በቴሌ ክላውድ መሰረተ-ልማት ላይ የተገነባ መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት፣ ደንበኞች እጅግ ጥራት ያላቸውን ከ60 በላይ የቀጥታ ስርጭት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችንና ከ350 በላይ ቪዲዮዎችን ያለ ሳተላይት ዲሽ በቤት ውስጥ የዋይ-ፋይ (Wi-Fi) አማካኝነት በቀላሉ እንዲያገኙ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
ወይዘሪት ፍሬህይወት አክለውም፣ ኩባንያው የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና የደንበኞችን ተሞክሮ ለማሳደግ የሚያስችለውን “ንክኪ-አልባ” የዲጂታል አሠራር መተግበሩን ገልጸው፣ ይህም ደንበኞች ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ሳይሄዱ በኦንላይን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።
በተጨማሪም የ“ኮፐር ስዊች-ኦፍ” ፕሮጀክትን በማፋጠን እስካሁን ከ79 ሺህ በላይ ደንበኞችን ወደ ፋይበር ኢንተርኔት ማሸጋገር እንደተቻለና ይህም ደንበኞች እጅግ ፈጣንና አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ጠቁመዋል።
የቴሌስትሪም አገልግሎት ለቤተሰቦች፣ ለሆቴሎችና ለንግድ ተቋማት የተሻለ የዲጂታል መዝናኛ አማራጭ ይዞ መምጣቱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ አገልግሎቱ የሀገሪቱን የዲጂታል 2030 ራዕይ ከግብ ለማድረስ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አረጋግጠዋል።
📷 ከበደ መክብብ #ethiotelecom #telestream #digitalethiopia #fiberbroadband #techinnovation #zerotouch #telecloud #ethiopiadigital2030

Comments