20 days ago
ዳኛ ከተጫዋች በተጨማሪ ደጋፊ የሚቀጣበት ዘመን ደረሰ!
#ethiopia | ሮማኒያ የተመልካቾችን አላስፈላጊ ባህሪ ስድብና ጫና ለመግታት አዲስ "ጥቁር ካርድ" አስተዋወቀች።
የሮማንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታዳጊ ቡድኖች ላይ የሚታየውን የወላጆችና የተመልካቾችን አላስፈላጊ ባህሪ፣ ስድብና ጫና ለመግታት በሚል አዲስ "ጥቁር ካርድ" አስተዋውቋል።
ተመልካቾች ተጫዋቾችን፣ አሰልጣኞችን ወይም ዳኞችን መስደብና ማስፈራራት ሲጀምሩ ዳኛው ጨዋታውን አቁሞ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።
ድርጊቱ ከቀጠለ ጨዋታው ለ10 ደቂቃ ተቋርጦ ቡድኖች ወደ መልበሻ ክፍል እንደሚገቡም ይገልጻል።
ከእረፍት በኋላም ተገቢ ያልሆነው ባህሪ ካልቆመ ዳኛው "ጥቁር ካርድ" በማሳየት ጨዋታውን ሙሉ በሙሉ ይሰርዘዋል ማለት ነው።
የሕጉ ዋና ዓላማ ታዳጊዎች ከአዋቂዎች ያልተገባ ውጥረትና ስድብ እርቀው ነፃ ሆነው በስፖርቱ እንዲደሰቱ ማድረግ ነው ተብሏል።
ብጫ ካርድ ያስጠነቅቃል፣ ቀይ ካርድ ከሜዳ ያሰናብታል፤ ጥቁር ካርድ ደግሞ ከሜዳ ውጭ ላለው ስርዓት አልበኝነት የመጨረሻው መፍትሔ ሆኗል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #romaniafootball #blackcard #youthfootball #footballnews

7 months ago
በቦሌ ክፍለ ከተማ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ድግስ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ
#ethiopia | የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከ"ከነዓን የስፖርት ትጥቅ አምራች" ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 4ኛው ዙር የበጋ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር በዛሬው ዕለት (የካቲት 28/2018 ዓ.ም) በወረዳ 5 "24 ሜዳ" በድምቀት ተጀምሯል።
የውድድሩ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ተሳታፊዎች፦
ከ1,000 በላይ ታዳጊዎች እና 44 ቡድኖች።
የዕድሜ እርከን፦
ከ13፣ ከ15 እና ከ17 ዓመት በታች።
ቆይታ፦
እስከ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም (ለሁለት ወራት)።
የከነዓን የስፖርት ትጥቅ አምራች ሚና፦
ድርጅቱ ባለፉት 3 ዓመታት ከ600 በላይ ለሚሆኑ ክለቦች ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የዚህ ታላቅ ውድድር ዋና ደጋፊ በመሆን ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል። የድርጅቱ ባለቤት አቶ ከነዓን ሰሎሞን እንደገለጹት፣ ድርጅቱ ለአሸናፊዎች እና ከፍተኛ ተሰጥኦ ላላቸው ታዳጊዎች ልዩ ሽልማቶችን ያዘጋጀ ሲሆን ለሀገራችን ስፖርት ዕድገት ደማቅ አሻራ ለማስቀመጥ እየሰራ ይገኛል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ እና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዳግም ጣሰው ውድድሩ ለጤናማ ትውልድ ግንባታ ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል።
በዕለቱ የተገኙት ታዋቂው አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እንዲህ ያሉ ውድድሮች ለብሔራዊ ቡድን ተተኪ ለማፍራት መሠረት መሆናቸውን መስክረዋል።
📍 ቦታ፦ ቦሌ ወረዳ 5 (24 ሜዳ)
🙌 ሁላችሁም እየመጣችሁ ታዳጊዎቹን እንድታበረታቱ ጥሪ ተላልፏል!
#bolesports #kenaansportswear #youthfootball #ethiopianfootball #healthygeneration

Comments