21 days ago
ዳኛ ከተጫዋች በተጨማሪ ደጋፊ የሚቀጣበት ዘመን ደረሰ!
#ethiopia | ሮማኒያ የተመልካቾችን አላስፈላጊ ባህሪ ስድብና ጫና ለመግታት አዲስ "ጥቁር ካርድ" አስተዋወቀች።
የሮማንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታዳጊ ቡድኖች ላይ የሚታየውን የወላጆችና የተመልካቾችን አላስፈላጊ ባህሪ፣ ስድብና ጫና ለመግታት በሚል አዲስ "ጥቁር ካርድ" አስተዋውቋል።
ተመልካቾች ተጫዋቾችን፣ አሰልጣኞችን ወይም ዳኞችን መስደብና ማስፈራራት ሲጀምሩ ዳኛው ጨዋታውን አቁሞ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።
ድርጊቱ ከቀጠለ ጨዋታው ለ10 ደቂቃ ተቋርጦ ቡድኖች ወደ መልበሻ ክፍል እንደሚገቡም ይገልጻል።
ከእረፍት በኋላም ተገቢ ያልሆነው ባህሪ ካልቆመ ዳኛው "ጥቁር ካርድ" በማሳየት ጨዋታውን ሙሉ በሙሉ ይሰርዘዋል ማለት ነው።
የሕጉ ዋና ዓላማ ታዳጊዎች ከአዋቂዎች ያልተገባ ውጥረትና ስድብ እርቀው ነፃ ሆነው በስፖርቱ እንዲደሰቱ ማድረግ ነው ተብሏል።
ብጫ ካርድ ያስጠነቅቃል፣ ቀይ ካርድ ከሜዳ ያሰናብታል፤ ጥቁር ካርድ ደግሞ ከሜዳ ውጭ ላለው ስርዓት አልበኝነት የመጨረሻው መፍትሔ ሆኗል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #romaniafootball #blackcard #youthfootball #footballnews

Comments