26 days ago
እናት! ቃላት የማይገልጿት...
************
ዓለም ብዙ ቋንቋዎች አሏት፤ ነገር ግን በሁሉም ቋንቋዎች ውስጥ ትርጉሙ የማይለወጥና ድምፀቱ የማይቀየር አንድ ጣፋጭ ቃል አለ... 'እናት'!
እናት ማለት ተራ ቃል አይደለም። መዝገበ ቃላት ሊፈቱት የማይችሉት ረቂቅ ትርጉም ነው፤ እናት የሕይወት መጀመሪያ፣ የፍቅር ምንጭ እና የጽናት ተምሳሌት ናት፡፡
ራስን በመርሳት ለሌላ ሰው መኖር የሚችል ማን አለ? የገዛ ህመምን ደብቆ የልጅን ሳቅ መምረጥ፣ የራስን ረሃብ ችላ ብሎ ለልጅ ማብላት... እነዚህ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች በሙሉ ለእናቶች ተችለዋል፡፡
እናት ማለት በጨለማ ውስጥ ብርሃን የምትሆን፣ በድካም ውስጥ ብርታት የምትሰጥ፣ እንዲሁም ዓለም ፊቷን በምታዞርበት ሰዓት እጆቿን ዘርግታ የምትቀበል ብቸኛ መጠጊያ ናት።
በየዓመቱ የፈረንጆቹ ግንቦት ወር በገባ በሁለተኛው እሁድ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን፣ የእናትነትን ክብር እንዲሁም እናቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን የማይተካ ሚና ለማድነቅና ዕውቅና ለመስጠት የሚከበር ልዩ ቀን ነው፡፡
ይህ ቀን እናቶች ለልጆቻቸው እና ለቤተሰባቸው የሚከፍሉትን መስዋዕትነት የምናስብበትና ምስጋናችንን የምንገልጽበት ግሩም አጋጣሚ ነው፡፡
እስቲ ዛሬ ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ... ለዚህች እናት የሚመጥን ምን ምላሽ ሰጠናት? ውድ ስጦታ ላያስፈልጋት ይችላል፤ ነገር ግን መልካም ሰው ሆነን የድካሟን ፍሬ አሳይተናት ይሆን? አንድ "እወድሻለሁ!" የሚል ቃል፣ አንድ የፍቅር እቅፍ፣ ወይም ደግሞ ስለ ህልውናዋ የምናቀርበው ምስጋና ለእርሷ ትልቅ ትርጉም አለው።
እናት ማለት የፍቅር ትርጓሜ፣ የቤታችን ምሰሶ እና ቃላት የማይገልጿት ሕያው የፍቅር ትእምርት ናትና በየቀኑ ልናከብራት ይገባል፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን ነገ (እሁድ) ይከበራል፡፡ ለመሆኑ ለእናቶቻችን ምን ስጦታ አዘጋጅተናል? ምን ዓይነት የፍቅር ቃልስ ልንነግራቸው ወስነናል? እናቶቻችን የከፈሉልንን ዋጋስ በሚገባ አስበንበታል? እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችንን እየጠየቅን የውድ እናቶቻችንን ውለታ ለማሰብ እንዘጋጅ!
መልካም የእናቶች ቀን!
በሄዋን ጌታቸው
#mothersday #happymothersday #unconditionallove #mothersday2026 #loveformom