2 months ago
የኦሮሚያ ሻይ ኢኒሼቲቭ የሻይ ልማትን ከተራ የእርሻ ምርትነት ወደ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ አቅምነት እየቀየረው ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ
***************
የኦሮሚያ ሻይ ኢኒሼቲቭ የሻይ ልማትን ከተራ የእርሻ ምርትነት ወደ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ አቅምነት እየቀየረው መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ሀብት መኖር ብቻውን ብልጽግናን እንደማያረጋግጥ ጠቅሰው፣ ሀብትን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ አቅም ለመቀየር የቴክኖሎጂ፣ የፋይናንስ፣ የኢንቨስትመንትና የገበያ ትስስርን ያካተተ ጠንካራ የእሴት ሰንሰለት መዘርጋት መቻሉን አስታውቀዋል።
እስከ 2013 ዓ.ም. ድረስ በክልሉ የነበረው የሻይ ልማት ከሚገባው ደረጃ እጅግ ያነሰ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሽመልስ፣ ችግሩ የምቹ አየር ንብረት ወይም የመሬት እጥረት ሳይሆን ሀብቱን ወደ ተወዳዳሪ እና ስትራቴጂያዊ ምርት የመቀየር የአቅም ውስንነት እንደነበር አስረድተዋል።
በአሁኑ ወቅት ግን በኦሮሚያ ሻይ ኢኒሼቲቭ አማካይነት መሬት፣ አርሶ አደር፣ የሻይ ችግኝ፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ በአንድ የምርት ሥርዓት ውስጥ ተሳስረው አዲስ የገጠር ኢኮኖሚ ሥርዓት መሠረት እየተጣለ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚሁ መሠረት የሻይ ፋብሪካዎች እና ከምርት አሰባሰብ እስከ ማሸግ እና ስያሜ መስጠት ያለው የእሴት ሰንሰለት በስፋት እየተገነባ ይገኛል።
ኢኒሼቲቩ ከአንድ ተክል ልማት ባለፈ ለአርሶ አደሩ አዲስ የገቢ ምንጭ፣ ለወጣቶች እና ለሴቶች የሥራ እና የኢኮኖሚ ዕድል፣ ለኢንቨስተሮች ደግሞ አዲስ የገበያ አማራጭ መፍጠሩ ተገልጿል።
ለሀገር አቀፍ ኢኮኖሚም የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ የወጪ ንግድ ምርቶችን በማብዛት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።
በቅርብ ጊዜ ውስጥም ከኦሮሚያ የሻይ ክላስተሮች የሚመነጩት "ሆቤ ሻይ"፣ "ጮራ ሻይ" እና "ገፈሬ ሻይ" የተሰኙ ብራንዶች በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ መታየት እንደሚጀምሩ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በኢሉ አባቦራ፣ በቡኖ በደሌ እና በጅማ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮችም በዚህ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ በስፋት እየተሳተፉ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ የኦሮሚያ ሻይ ኢኒሼቲቭ የሻይ ቅጠልን ከማምረት ባሻገር አዲስ የኢኮኖሚ አቅም እያበቀለ የሚገኝ የገጠር ኢኮኖሚ መዋቅር ሽግግር ማሳያ መሆኑን አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመልዕክታቸው አጽንዖት ሰጥተዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #oromia #teafarm #ebc

Comments