5 months ago
የ60 ሚሊዮን ብር የዲጂታል ሎተሪ ባለዕድለኞች ሽልማታቸውን ተረከቡ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሎተሪ ታሪክ ውስጥ ግዙፍ የተባለውን 60 ሚሊዮን ብር ጨምሮ የሌሎች ከፍተኛ ሽልማቶች የዕጣ አወጣጥ እና የሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት በስካይላይት ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።
👉 አቶ ብርሃኑ ጎበዜ (ከባሌ ጎባ ከተማ) የ60 ሚሊዮን ብር አሸናፊ
👉 አቶ ማስረሻ መላኩ (ከአዲስ አበባ) የ20 ሚሊዮን ብር አሸናፊ
👉 አቶ ብዙነህ ታደሠ (ከቢሾፍቱ ከተማ) የ10 ሚሊዮን ብር አሸናፊ
በተጨማሪም 12 ዕድለኞች እያንዳንዳቸው የ1 ሚሊዮን ብር ባለቤት ሆነዋል።
ባለፉት ሦስት ወራት ከጥቅምት 9 እስከ ጥር 9 በቆየው በዚህ የዲጂታል ሎተሪ መርሃ-ግብር ላይ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በኢትዮ ሎተሪ ድረ-ገጽ፣ በቴሌ ብር፣ በ8989 አጭር የፅሁፍ መልዕክት (SMS) እና በባንኮች አማካኝነት በቤታቸው ሆነው ዕድላቸውን ሲሞክሩ ቆይተዋል።
በዚህ መርሃ-ግብር ለአሸናፊዎች ከተበረከተው ገንዘብ ባሻገር የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን በመተባበር ለሶስት መንግስታዊ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ አበርክተዋል።
በዚህም መሰረት፡
📍 ለባሌ ሮቤ ከተማ አቅመ ደካሞች የጤና መድህን 1.8 ሚሊዮን ብር፣
📍 ለአዲስ አበባ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 2 ሚሊዮን ብር፣
📍 ለአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 2.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የዲጂታል ሽግግር፣ ደህንነቱና ግልፅነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ አሰራር መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
#ethiopianlottery #digitallottery #bigwin #tamconsoftware #ethiopia #techinnovation #8989sms #telebirr #socialresponsibility #addisababa

Comments