5 days ago
እናት ባንክ የGABV የአፍሪካ ቀጠና ዓመታዊ ስብሰባን በአዲስ አበባ እያስተናገደ ነው
#ethiopia | እናት ባንክ የዓለም አቀፍ እሴት መር ባንኮች ህብረት (GABV) የአፍሪካ ቀጠና ዓመታዊ ስብሰባን በአዲስ አበባ እያስተናገደ ነው።
“የባንክ ሥርዓትን መለወጥ፤ የአካባቢ፣ የማህበራዊና የአስተዳደር መርሆችን እና ቴክኖሎጂን ለፋይናንስ ተጽዕኖ ማዋል” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ስብሰባው መስከረም 21 እና 22 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን፣ የGABV የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባ በኢትዮጵያ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያ መሆኑ ተገልጿል።
የእሴት መር ባንክ አሠራር የፋይናንስ ተቋማት የኢኮኖሚ ጥቅምን ብቻ ሳይሆን ማህበራዊና አካባቢያዊ ተጽዕኖንም በማገናዘብ ዘላቂ እና ረጅም ጊዜ የሚያስገኝ እሴት ለመፍጠር የሚያተኩር የባንክ አሠራር ነው።
GABV በ45 አገራት የሚገኙ ከ70 በላይ የባንክና የፋይናንስ ተቋማትን ያሰባስባል። በአፍሪካ ቀጠናውም ከኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ጋና የተውጣጡ ዘጠኝ ባንኮች ተሳታፊ ናቸው። እነዚህ ባንኮች በጋራ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞችን እንደሚያገለግሉ፣ ወደ 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሀብት እንደሚያስተዳድሩና 15 ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞችን እንደሚያሰማሩ ተገልጿል።
የዘንድሮው የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ የባንክና የፋይናንስ ተቋማት መሪዎችን፣ የልማት ፋይናንስ አጋሮችን፣ ተቆጣጣሪዎችንና የዘርፉን ባለሙያዎች በአንድ መድረክ አሰባስቧል። ተሳታፊዎቹም የአፍሪካ የባንክ ዘርፍ እየተጋፈጣቸው ባሉ ዕድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ልምድና ሀሳብ እየተለዋወጡ ነው።
በስብሰባው ከሚመከሩ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የሳይበር ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ እውቀት፣ ዲጂታል ለውጥ፣ የዘላቂነት ሪፖርት አያያዝ እና ለታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ፋይናንስ መስጠት ይገኙበታል።
የGABV ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርቲን ሮነር ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ልማት አዲስ ምዕራፍ ውስጥ እየገባች መሆኗን ጠቁመው፣ በዘርፉ የሚካሄዱ ማሻሻያዎች ለአዳዲስ ዕድሎችና ለበለጠ ውድድር መንገድ እየከፈቱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፈጠራን፣ አካታችነትንና የረጅም ጊዜ እሴት መፍጠርን የሚያጣምሩ የባንክ አሠራሮች እንደሚያስፈልጉም አመልክተዋል።
የእናት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰሎሞን በበኩላቸው፣ ባንኩ የተመሰረተው በኢትዮጵያ ሴቶችና ቤተሰቦች የፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋት የኢኮኖሚ ዕድል ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል። የእሴት መር የባንክ አሠራርና ዘላቂ የንግድ እድገት ተቃራኒ ጉዳዮች ሳይሆኑ ተደጋጋፊ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
እናት ባንክ በ11 ራዕይ ባላቸው ሴቶች የተመሰረተ ሲሆን፣ ከመጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የባንክ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ባንኩ ከ24 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖችና ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ንቁ ደንበኞች እንዳሉት ሲገለጽ፣ በመላ አገሪቱ 225 ቅርንጫፎችን በመክፈት ዘመናዊ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችንም እያቀረበ ይገኛል።
የሁለት ቀናት የGABV የአፍሪካ ቀጠና ስብሰባ በኢትዮጵያ ከሚካሄደው የፋይናንስ ዘርፍ ለውጥ ጋር የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የባንክ ተቋማትን ልምድ ለማገናኘት፣ ትብብርን ለማጠናከር እንዲሁም በፈጠራ፣ በዲጂታል ለውጥ፣ በአካታች ፋይናንስና በዘላቂ ፋይናንስ ዙሪያ የጋራ ልምድ ለመፍጠር ያለመ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#enatbank #gabv #ethiopia #banking #finance #digitaltransformation #financialinclusion #sustainablefinance

Comments