1 month ago
"My Seed" የተሰኘ የሞባይል ስልክ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ!
#ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ «ቲቸር ዳኒ» በሚል ስሙ የሚታወቀው መምህር ዳኛቸው ሻምበል፣ ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በስልካቸው በቀላሉ ትምህርት የሚከታተሉበትን "My Seed" የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን ገለጸ።
መተግበሪያው በተለይም ከአምስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ እኩል የትምህርት እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጿል።
በላይ የተጫነው ይህ መተግበሪያ ተማሪዎች የሀገሪቱን የትምህርት ካሪኩለም መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን አሰልቺ ባልሆነና ልክ እንደ ፊልም የተቃኙ ማራኪ ቪዲዮዎች አማካኝነት እንጅ በማድረግ እንዲማሩ ተደርጎ የተቃኘ ነው።
ከተለመዱት የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ የመንፈስ ጥንካሬና አስተሳሰብን የሚያጎለብቱ የማይንደሴት ስልጠናዎችን እንዲሁም ተማሪዎች ወደፊት መሆን የሚፈልጉትን ሙያ እንደ ዶክተር ኢንጂነርና ፓይለት የመሳሰሉትን እንዲረዱ የሚያስችሉ ትምህርቶችን አካቷል።
አፕሊኬሽኑ በአሁኑ ወቅት በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ወደፊትም እያንዳንዱ ተማሪ በአፍ መፈቻ ቋንቋው እንዲማር ለማስቻል በሌሎች አራት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
አፕሊኬሽኑን ተጠቃሚ ለማድረግ በቀረበው እቅድ መሰረት ተማሪዎች በወር 399 ብር ክፍያ በመፈፀም ሁሉንም የትምህርት አይነቶች ማስታወሻዎችንና የልምምድ ጥያቄዎችን ማግኘት ይችላሉ።
በተጨማሪም በኔትወርክ ችግር ምክንያት የዳታ እጥረት እንዳይገጥማቸው ቪዲዮዎችን አንድ ጊዜ ዳውንሎድ በማድረግ ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መከታተል የሚችሉበት አሰራር የተዘረጋ ሲሆን በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ዳታ በማይስፈልግበት መልኩ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን መምህር ዳኛቸው አስታውቋል።
ተማሪዎችን ለማበረታታትም በአመቱ መጨረሻ የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተጠቃሚዎችን በልዩ መስፈርት በመምረጥ የመኪና ሽልማት የሚያበረክት "መማር ያሸልማል" የተሰኘ ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#english #education #myseed #teacherdanny #amharic #ethiopia #learningapp #digitaleducation #elearning #studymotivation

Comments